Translation is not possible.

አሜሪካ ለእስራኤል 2,000 ፓውንድ የሚመዝን Bunker buster የተሰኘን እጅግ አደገኛ ቦንብን ጨምሮ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ወደ እስራኤል ልካለች ።

ሁለት ወር በተጠጋው ጦርነት እስራኤል በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክማ ታይታለች ። የመሳሪያ ክምችቷ እየተመናመነ የወታደሮቹ ሞራል ሲነኳኮትና እዟ ሲበታተን ተስተውሏል። ይህ ኪሳራ ያፍረከረካት እስራኤል የአንድ ሳምንት የተኩስ አቁም ለማድረግ መገደዷ ይታወቃል ።

ታዲያ አሜሪካ ይህንን ተመልክታ የእስራኤልን የመሳሪያ መመናመን ለማሟላት ቢሊዮን ዶላሮች የተከሰከሰባቸውን እጅግ ውድ ቦንቦቿን ወደ እስራኤል ልካለች ። በዚህም መሰረት 15,000 ከአይሮፕላን የሚጣሉ ቦንቦች ፤ 57,000 የመድፍና የከባድ መሳሪያ ተተኳሾችን ፤ 5,000 Mk82 ቦንቦችን ፤ 5,400 Mk84 ቦንቦችን ፣ 1,000 GBU -35 እንድሁም 3,000 JDAMS ቦንቦችን ወደ እስራኤል ልካለች ።

ከሁሉም እጅግ አደገኛው መሳሪያ ግን Bunker buster የተሰኘው ቦንብ ነው ። ይህን ቦንብ ለመጀመሪያ ጊዜ የሰራቺው በሁለተኛው የአለም ጦርነት ወቅት ጀርመን ነበረች ። የቦንቡ አላማም ከምድር ውስጥ ያሉ ምሽጎችን ሰርስሮ ገብቶ እንዲያፈራርስ ነው ።

Bunker Buster ቦምብ ሲተኮስ ከፊት ያለን ከባድ ምሽግ ወይንም ኮንክሪት ሳይፈነዳ ከሾለከ በሗላ እንዲፈነዳ ተደርጎ የተሰራ ነው ። ይህንን አደገኛ መሳሪያ አሜሪካ በአፍጋኒስታን ወንድሞቻችን ላይ ስትጠቀመው ኖራለች መጨረሻዋን ከሽንፈት ባይታደገውም !!

ዛሬም እስራኤል ይህንን መሳሪያ በጋዛ ላይ ትጠቀመው ዘንዳ አሜሪካ አስታጥቃታለች ። የፍልስጤም ህፃናትም በአሜሪካ አስታጣቂነት በእስራኤል ተኳሽነት እያለቁ ነው ።

በርግጥ ለእስራኤል አሜሪካ አለቻት !

ለፍልስጤማውያን ግን ከአላህ ውጭ ማንም የላቸውም ! እርሱም የሀያሎች ሁሉ ሀያል ነውና ይደርስላቸዋል !!!

#seid_mohammed_alhabeshiy

ቴሌግራም

👉 t.me/Seidsocial

Send as a message
Share on my page
Share in the group