Translation is not possible.

የምቀኝነት ጥግ

ሀቢል እና ቃቢል የተሰኙት የአድም ልጆች አስደማሚ ታሪክ

ጌታችን አላህ ጥራት ይገባውና አባታችን አደምን(ዐ.ሰ) ከጭቃ ፈጥሮ እናታችንን ሀዋን ከአደም(ዐ.ሰ) ከጎኑ ካስገኘ በኋላ በጀነት በተድላ እንዲኖሩ አደረጋቸው። አንዲትን ቅጠልም እንዳይቀርቡ በጥብቅ አዘዛቸው። የአላህ እርግማን በርሱ ላይ ይሁንና የምንግዜም የአደም(ዐ.ሰ) እና ልጆቹ ግልፅ ጠላት የሆነው ኢብሊስ አሳስቶ ይህን የተከለከሉትን ተግባር እንዲፈፅሙ በማድረግ ከጀነት ወደ ምድር እንዲወርዱ አስደረጋቸው።

አደም(ዐ.ሰ) እና ባለቤቱ ሃዋ ምድር ላይ መኖር ከጀመሩ ሰነባብተዋል። በጣም ብዙ ልጆችንም አፍርተዋል። ሃዋም በምትወልድ ጊዜ መንታ ነበር የምትወልደው አንድ ወንድ እና አንድ ሴት። ኋላ ላይም ለትዳር ሲደርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ከሌላኛው ልጅ ጋር አብራ የተወለደችውን ነው የሚያገባው። ከሱ ጋር አብራ የተወለደችውን ደግሞ እርሱ ያገባት ልጅ ጋር አብሮ የተወለደው ልጅ ያገባታል። ከራሱ ጋር አብራ የተወለደችውን ልጅ ማግባት አይችልም።

ከአደም(ዐ.ሰ) ልጆች ውስጥ ቃቢል እና ሀቢል የተባሉ አሉ። ቃቢል በግብርና ስራ የሚተዳደር አርሶ አደር ሲሆን ሀቢል ደግሞ በእንስሳት እርባታ ሚተዳደር አርብቶ አደር ነው።

ከቃቢል ጋር አብራ የተወለደችው ልጅ በጣም ቆንጆ እና መልከ መልካም ናት። ከሀቢል ጋር የተወለደችው ግን መልኩዋ እንብዛም ነበር። ለትዳር በደረሱም ጊዜ አባታቸው አደም(ዐ.ሰ)  ሀቢል የቃቢልን ቃቢል ደግሞ የሀቢልን እህት(አብራ የተወለደች) እንዲያገቡ አዘዛቸው። ቃቢልም የራሱን እህት ማግባት ፈልጎ ነበር እና ይህን ሲሰማ በጭራሽ አይሆንም አለ። እህቴን(ከኔ የተወለደችውን) እኔ እራሴ ነው ማገባት አለ። አደምም(ዐ.ሰ) እንዲተው ቢነግረው ሊሰማ አልቻለም አሻፈረኝ አለ። በዚህን ጊዜ አደም(ዐ.ሰ) መፍትሔ ይዞ መጣ። ሁለቱም ምፅዋት እንዲያቀርቡ እና ምፅዋቱ ተቀባይነት ያገኘ ለርሱ ሊፈረድለት እና ልጅቱዋንም ሊያገባ ተስማሙ። ቃቢል ከንብረቱ የማይፈልገውን ቆሻሻ የሆነ ሰብል ይዞ ሲመጣ ሀቢል ግን ከንብረቱ ውስጥ በጣም የሚወዳትን ሙክት በግን አቀረበ። ከዛም ከሰማይ እሳት ወርዳ የሀቢልን ይዛው ስትሄድ የቃቢልን ምንም ሳትነካ ተወችው። ቃቢልም እጅጉን ተበሳጨ። ወደ ሀቢልም በመዞር ያንተ ምፅዋት ተቀባይነት አገኘ የኔ አላገኘም እህቴንማ አታገባም እገድልሀለሁ ብሎ ዛተበት። ቃቢልም ታድያ አላህ ሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆች(አላህን ፈሪ ከሆኑ አካላት) ነው ብሎ መለሰለት።

{ وَاتْلُ عَلَيْهِمْ نَبَأَ ابْنَيْ آدَمَ بِالْحَقِّ إِذْ قَرَّبَا قُرْبَانًا فَتُقُبِّلَ مِنْ أَحَدِهِمَا وَلَمْ يُتَقَبَّلْ مِنَ الْآخَرِ قَالَ لَأَقْتُلَنَّكَ ۖ قَالَ إِنَّمَا يَتَقَبَّلُ اللَّهُ مِنَ الْمُتَّقِينَ}

በነርሱም ላይ የአደምን ሁለት ልጆች ወሬ ቁርባንን ባቀረቡና (አላህ) ከአንደኛቸው ተቀብሎ ከሌላው ባልተቀበለ ጊዜ (የኾነውን) በእውነት አንብብላቸው፡፡ «በእርግጥ እገድልሃለሁ» አለው፡፡ (ተገዳዩ) «አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው» አለ፡፡

                     [አል-ማኢደህ:27]

👉አላለቀም ኢንሻአላህ ይቀጥላል............

=-=-=-=

whatsApp

https://whatsapp.com/channel/0....029Va9evBFFy7269vAij

Ummalife

https://ummalife.com/marufabadir

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group