Translation is not possible.

〰〰😘 #እናት! 😘〰〰〰

✔️በኡመር ረ.ዐ ዘመን ነው አንድ ሠውዬ እናቱን ሀጅ ሊያስደርጋት ከየመን መካ ድረስ ተሸክሟት ይመጣል ።

አስቡት መኪና በሌለበት አውሮፕላን ባልታሰበበት ዘመን እናቱን በጀርባው ተሸክሞ ከ2.000ኪሎ ሜትር በላይ ዳገቱን ቁልቁለቱን ተራራውን አቋርጦ መካ ድረስ መምጣት? በዛ ላይ ሰውየው ምን እንዳለ ታውቃላችሁ?

〰〰〰〰… "በአላህ ይሁንብኝ ግመሎች ሁሉ መንገዱን ቢፈሩት እኔ ግን አልፈራሁትም "… ይል ነበር ።

ጉዞውን ጨርሶ መካ ሲገባ የአማኞች መሪ (ኡመር ኢብኑልህጣብን )ረ.ዐ ያገኛቸዋል።

⭐️ከጀርባው እናቱን እንደተሸከመ ሳያወርዳት ውስጡ ያለውን ጥያቄ ጠየቃቸው

…" አንቱ የአማኞች መሪ ሆይ አሁን የእናቴን ሀቅ አልተወጣሁምን ? "…ማለት ይጠይቃቸዋል ።

ኡመር ኢብኑል ህጣብ የሰውየውን ድካም ቢረዱም የሠጡት መልሥ ግን አስገራሚ ነበር ።

〰〰〰🍃" በአላህ ይሁንብኝ አንተን ለመውለድ ስታምጥ አንድ ጊዜ የተጨነቀችውን አይሆንም ወይም አንድጊዜ እንቅፋት ሲመታህ የተጨነቀችውን አይታካም " በማለት ነበር የመለሡለት ።

‼️ሱብሀን አላህ !!!

አስተውል ጀነት ያለው በእናት እግር ሥር ነው

"ወደ መልካም ነገር  ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)

@yasin_nuru <> @yasin_nuru

Send as a message
Share on my page
Share in the group