Translation is not possible.

ተረባርበን ይህን ስርአት እናሲዝ

..........

#update : የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያው ላይ በድጋሜ ማስተካከያ ማድረጉን ገለጸ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአገልግሎት ክፍያዎቹ ላይ በድጋሜ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። ማሻሻያው ባንኩ ከደንበኞቹ አገኘውት ባለው ግብረ መልስ መሰረት የተደረገ መሆኑን ነው የገለጸው።

በዚህም፦

- #በወዲአህ በተከፈቱ ሂሳቦች በቅርንጫፍም ሆነ በሞባይል ባንኪንግ የሚደረግ ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አግልግሎት ከክፍያ ነፃ ሆነዋል፤

- #በሙዳራባህ ውል የተከፈቱና እና ለረጅም ጊዜ ያልተንቀሳቀሱ ሂሳቦች (Inactive Accounts) ከክፍያ ሆነዋል።

- በቅርንጫፍ የሚከናወን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት ክፍያ እንደሚከተለው ተሻሽሏል

• ከብር 1 እስከ 10,000 =  5 ብር

• ከብር 10,000 እስከ ብር 100,000 = 10 ብር

• ከብር 100,001 በላይ = 10 ብር ሲደመር በእያንዳንዱ 100 ሺ 5 ብር (ከ100 ብር ያልበለጠ) ሆኗል።

- በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ወደ ሌላ ባንክ ወደሚገኝ ሂሳብ ገንዘብ ለማስተላለፍ ( #rtgs ) 50 ብር የአገልግሎት ክፍያ ያስከፍላል፤

- ከ P2P የገንዘብ ዝውውር በ ኢትስዊች (ETSWITCH) 5 ብር እና የኢትስዊች ክፍያን በመደመር የአገልግሎት ክፍያ ይከፈልበታል፤

- ወደ ሲቢኢ ብር ሂሳብ ከ50 ብር በታች ለማስገባት የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ የለም፤

- በሲቢኢ ብር በቀን ከ3 ጊዜ በላይ የገንዘብ ልውውጥ ሲኖር ገንዘብ የማስገባት አገልግሎት እንደሚከተለው የአገልግሎት ክፍያ ይታሰብበታል፡

• ከብር 50 በታች = ነፃ

• ከብር 51 እስከ ብር 500 = 6.45 ብር

• ከብር 501 እስከ ብር 2,000 = 7.60 ብር

• ከብር 2,001 እስከ ብር 3,000 = 8.18 ብር

• ከብር 3,001 እስከ ብር 4,000 = 9.33 ብር

• ከብር 4,001 እስከ ብር 5,000 = 10.48 ብር

• ከብር 5,001 እስከ ብር 6,000 = 11.63 ብር

• ከብር 6,001 በላይ ከሆነ ከሚገባው ገንዘብ 0.2 በመቶ እንዲሆን መወሰኑን ባንኩ አስታውቋል።

👋  @TikvahethMagazine

Send as a message
Share on my page
Share in the group