Çeviri imkansız.

ያልተወሱ ታሪኮች

=======

የአላህ መልእክተኛ(ﷺ) ከሞቱ በኋላ እስልምና ከአረብ ደሴት አልፎ በምእራብ እስከ አውሮፓ በምስራቅ እስከ ቻይና ድንበር ደርሷል።ከረሱል (ﷺ) ሞት በኋላ ሙስሊሞች አውሮፓ ለመግባትና ስፔንን ለ700 አመት ማስተዳደር ለመቻል 80 አመት ብቻ ነው የወሰደባቸው።

ታድያ ግን ሙስሊሞች በተቆጣጠሩዋቸው ቦታውች ላይ የሀገሬውን ሰዎች ቅርስና ስራዎቻቸውን ጠብቀው አቆይተዋል።ነገር ግን የሙስሊም ስርወ-መንግስት በተዳከመ ጊዜ መስሊሞች ያበረከቱትን ስራ እና በጣም ብዙ የተራቀቁ የሳይንስ ግኝቶችን እነዚህ ካሃድያን አውድመዋቸዋል። ሞንጎሎች የኢስላም የሳይንስ ማዕከል የነበረችውን ባግዳድን በጣም አፀያፊ በሆነ መልክ ድምጥማጡን አጥፋተዋል። ስፔኖችም የሙስሊሞችን ቅርስ አውድመዋል።

የኢስላም ስርወ-መንግስት ለአንድ ሺ አመት ያህል በአለም ሀያልና የሰለጠነ መንግስት ሆኖ ቆይቶዋል።አረብኛ አለምአቀፋ የትምህርትና የዲፕሎማሲ ቋንቋ ሆኖዋል። ሳይንስም ወደ መካከለኛው ምስራቅ አዘንብሎ ባግዳድ የሳይንስ መቀመጫ ለመሆን በቅታለች።

ሙስሊሞች በጣም ተክነውበት ከነበረና ስለ ስልጣኔያቸው ከሚጠቀሱት ዋነኛ የሆነው በህክምና የደረሱበት ምጥቀት ነበር።የኋላ ኋላ የኢስላም ስርወ-መንግስት ሲዳከም ምእራባውያን አብዛኛውን አጥፍተው ቀሪውን ወደ ቋንቋቸው ቀይረው የራሳቸው አስመስለዋል።

እኛ ሙስሊሞች አብዛኛው ታሪካችን ተቀምቶ እና ተሸፋኖ ይገኛል። ታሪካችንን አናውቅም የቀደምቶቻችን ጀብድ ዛሬ ለኛ ስንቅ ይሆነን ዘንድ አናወሳም። አላህ ፋቃዱ ከሆነ ሙስሊሞች የሰሩትን ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች በሳይንስና በህክምና የደረሱበትን ምጥቀት በክፋል ከፋፍዬ አቀርባለሁ። የትላንቶቹ መልካም ታሪክን ሰርተው አልፈዋል። ዛሬ ምድር ላይ የተተካን እኛ አላህ ጥሩ አሻራን አኑረው ከሚያልፋት ያድርገን።

ኡማ ላይፋ

======

ummalife.com/marufabadir

image
Mesaj olarak gönder
Sayfamda paylaş
Grupta paylaş