Translation is not possible.

በወንድማማቾች መካከል የጥላቻና በጎሪጥ የመተያየት ፍቱን መድኃኒት

———

በተለይ በዱኒያዊ ነገር ተጨቃጭቀህ ወደ ጥላቻና በጎሪጥ መተያየት ከመሄድ ተቆጠብ!!። የተጣላሀው ሰው ካለም የሚከተለውን ፍቱን መድኃኒት ወስደህ ነፍሲያህን አሸንፈህ ብትበደልም እንኳን ይቅር በል!፣ አላህ አንተን ስንት ነገር ይቅር ብሎሃል???

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል:-

«እርስበርስ ከመጠላላት በሚከተለው መልኩ መጥራት ይቻላል:-

በመጀመሪያ:- በዚህ መጠላላት ያለውን ወንጀል እና የሚያመልጠውን መልካም ነገር ማስታወስ ነው። ስራዎች እንኳን ወደ አላህ የሚቀርቡት ሰኞና ሀሙስ ነው፣ በሁለት ሰዎች መካከል ጥል ካለ አላህ “እነዚህ እስከሚታረቁ ድረስ ስራቸውን አቆዩት” ይላል። አምላካችን አላህ በአንተና በወንድምህ መካከል ጥል ካለ ሰኞና ሀሙስ የስራህን ውጤት አይመለከትልህም ማለት ነው።

ሁለተኛው:- ይቅር በማለትና በመታረቅ፣ ይቅር ባዩ ብዙ መልካም ነገር እንዳለው ማወቅ ነው። ይህ ይቅር ባይነቱ አሸናፊነትን/ክብርን እንጂ አይጨምርለትም። ልክ ነቢዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዳሉት:- “ለባሪያው ይቅር በባይነቱ አላህ አልጨመረለትም አሸናፊነትን ቢሆን እንጂ።” [ሙስሊም ዘግበውታል።]

ሶስተኛው:- ሸይጧን ጠላቱ እንደሆነና የጥላቻንና በጎሪጥ የመተያየትን እሳት በሙእሚኖች መካከል የሚያቀጣጥለው እሱ እንደሆነ ሊያውቅ ይገበዋል። ምክንያቱም ሸይጧን ሙስሊሞች ተዋደውና ተግባብተው ሲያይ ይተክዛል። ተበታትነው በመካከላቸው ጥላቻና በጎሪጥ መተያየትን ሰፍኖ ሲመለከት ይደሰታል።

ሰዎች በመጠላላትና በጎሪጥ በመተያየት ላይ ያለውን ጥቅምና ጉዳት በሚያስታውሱ ጊዜ ጥቅም ያለበትን በመያዝ ጉዳት ያለውን መተው ቅሮት የለውም!።

ነፍሲያህን በመታገል አደራ!! ምንም እንኳን ከላይ ሲታይ ያሳነስካት/ያዋረድካት ቢመስልህም በእውነቱ ግን አሸናፊ ታደርጋታለህ፣ ምክንያቱም ለአላህ ብሎ የተናነሰ አላህ ከፍ ያደርገዋልና አላህ ለባሪያው ይቅር ባይ በመሆኑ አሸናፊነትን እንጂ ሌላን አልጨመረለትም።

ይህን በተግባር ሞክረህ እየው! አንተ ይህን ባደረግክ ጊዜ ይቅር ካልክ በአንተና በወንድሞችህ መካከል ያለውን ነገር ካስተካከልክ በምቾትና በተረጋጋ ሁኔታ፣ በልብ መስፋትና ልብህ በደስታ የተሞላ ሆነህ ትኖራለህ። ነገር ግን በልብህ በነሱ ላይ ጥላቻ ካለ ነፍሲያህን በጭንቀትና በውጥረት ውስጥ ሆና ታገኛታለህ። ሸይጧን እየመጣ በሰውዬው ንግግር ላይ የተለያዩ መላምቶችን ይነግርሃል፣ ሸሪዓችን አንድ ሰው የወንድሙን ንግግር ሸር ቢመስለው እንኳን በመልካም መገመት እንዳለበት የደነገገ ከመሆኑም ጋር ሸይጧን ግን ሁሉንም በሸር እንዲጠረጥረው/እንዲያስበው ያደርገዋል።»

📝 [ሸርህ አል-ሙምቲዕ ዐላ ዛዲል ሙስተቅኒዕ 2/341]

አላህ ነፍሲያቸውንና ሸይጧንን አሸንፈው ይቅር ከሚባባሉት ያድርገን!!።

✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ

https://telegram.me/IbnShifa

https://telegram.me/IbnShifa

Send as a message
Share on my page
Share in the group