6 уйӑх Куҫарас
Çĕнĕ çулахне йывăçлăх

ፕሌክሰስ አግሮ ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማህበር በኢትዮጵያ ውስጥ የማህበረሰባችንን የሀይማኖትና ባህል እሴቶች የጠበቀ እጅግ ተአማኒ እና ተቀዳሚ የአክሲዮን ማህበር መሆንን መነሻ አድርጎ በመመስረት ላይ ያለ አክሲዮን ማህበር ሲሆን ይህንንም እውን ለማድረግ የሚያስችለውን እቅድ ቀርፆ መንቀሳቀስ ከጀመረ ወራቶችን አስቆጥሯል፡፡ በስነ ምግባር ላይ የታነጹ የስራ አመራር ስርዓቶችን በመከተል ትርፋማ የእርሻ እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ መሰማራትን አላማው አድርጓል።

ፕሌክሰስ አግሮ ኢንዱስትሪ አ.ማ የመጀመሪያው የሆነውን ግዙፍ የተቀናጀ የእንስሳት ማድለብያ፣ ሐላል ቄራና ስጋ ማቀነባበሪያ እንዲሁም የእንስሳት መኖ እርሻና ማቀነባበሪያ ላይ የፕሮጀክት አዋጭነት ጥናቱን በማጠናቀቅ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሲሆን  የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት ለማስፋት ሲባል የመደበኛ እና የመስራችነት ጥቅም የሚያስገኙ አክሲዮኖችን በመሸጥ ላይ ይገኛል። ከመጀመርያ ዙር ፕሮጀክቶች በተጨማሪ ማህበሩ ወደፊት አዋጭ የሆኑ የግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ አስመጪነትና ላኪነት የንግድ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት አልሞ እየሰራ ይገኛል። በመሆኑም የፕሌክሰስ አክሲዮን ድርሻዎትን በመግዛት በጠንካራ ህብረትና በላቀ ግብ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ድርጅት በአባልነት እንዲቀላቀሉ ስንጋብዞ በታላቅ ደስታ ነው።

አድራሻ: አየርጤና አደባባይ ከመገርቱ ህንፃ ጎን 3ኛ ፎቅ

ስልክ: 0906434444 | 0978095986

Email: plexusagroindustry@gmail.com

image
Хыпар пек ярас
Ман тетелӗ питра пайлас
Ушкӑнта пайлас