ማሻሻያው ማሻሻያ ይፈልጋል
~
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Commercial Bank of Ethiopia የአገልግሎት ክፍያ ላይ ማሻሻያ አድርጌያለሁ ብሎ አውጥቷል። ሊንኩን ከስር አያይዣለሁ። እንዴት ነው ወደናንተው ቅርንጫፍ በተላከ ብር የአገልግሎት የምንከፍለው? ብሩ ወደ ንግድ ባንክ መግባቱ በራሱ ለንግድ ባንክ ጥቅም አይደለም ወይ? በወለድ ነፃ ሂሳብ ውስጥ የሚገኘው ከ 100 ቢሊዮን በላይ ገንዘብ በእጃችሁ ላይ መሆን ለናንተ በቂ ጥቅም ስላልሆነ ነው የአገልግሎት ክፍያ የምትቆርጡት? ራሳችሁ ለምትጠቀሙበት ነው እኛ የምንከፍለው? ለሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚሆን ማካካሻ ሊኖራችሁ ሲገባ ጭራሽ ሌላ ነገር ትጨምራላችሁ?
በነገራችን ላይ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ጠንከር ያለ ድምፅ ቢያስተጋባ፣ ከድምፅም አልፎ የሚያስደነግጥ በተግባር የታገዘ እርምጃ ቢያስከትል ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ይችል ነበር። የተሻለ ገንዘብ ወይም ደንበኞችን ለመሰብሰብ በባንኮች መካከል በሚኖር ፉክክር የአገልግሎት ክፍያ የሚሉትን ዜሮ ማድረግ ይቻላል። በሚሰበስቡት ገንዘብ የሚያገኙት ጥቅም ከአገልግሎት ክፍያ በላይ ነውና።
ለንግድ ባንክ
* ማሻሻያችሁን አሻሽሉ።
* የወለድ ነፃ መስኮቶች ብዙ ቦታ ሁሉም መስኮቶች ተዘግተው በአንድ መስኮት ብቻ ሰው የሚጉላላበት ሁኔታን አስተካክሉ። በተለይ ይሄ ችግር ሆን ተብሎ በሚመስል በዒድ ዋዜማ ላይ ይጎላል።
* ሰራተኞቻችሁን ስርአት አስተምሩ። የሚመጣው ደንበኛ የራሱን ገንዘብ የሚወስድ ወይም በራሱ ገንዘብ የሚገለገል እንጂ ከነሱ እርጥባን ሊጠይቅ ፌስታል ይዞ የቆመ የኔ ብጤ እንዳልሆነ ንገሯቸው። ከኪሳቸው የሚሰጡን ነውኮ የሚመስሉት። የሰራተኞቹ ስርአት መቅለል ደግሞ ክፍለ ሃገር ላይ ይብሳል።
* ከምንም በላይ በራሳችሁ የሲስተም ችግር እና በሰራተኞቻችሁ ነውረኛ ተግባር ገንዘባቸውን እየተዘረፉ ያሉ ወገኖች ብራቸውን ባንኩ ራሱ ይተካ። የሰራተኛው መዝረፍ ማለት ቀጥታ ተቋሙን ነው የሚመለከተው። በተቋሙ ችግር ደንበኛ የሚጎዳበት ሂደት ፈፅሞ ልክ አይደለም።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor