Translation is not possible.

የእስራኤልና የሃማስን ዉል እንዴት አገኙት?

በስምምነቱ እስራኤል አትራፊ አይደለችምን?

~~~~~~~

.

“የ 6 ሰአቱ ቅጽበታዊ ጦርነት ባለቤት” በሚል የሚነገርላት ጽዮናዊቷ እስራኤል ለ 46 ቀናት ያህል የጋዛ ህጻናትና ያልታጠቁ ደካሞችን በሚሳዬል በቦምብና በአለም አቀፍ ደረጃ ክልክል በሆነው የፎስፈረስ ኬሚካል በጅምላ ስትገድል ከቆየች በኋላ ከሃማስ ጋር ጊዝያዊ ስምምነት አድርጋለች

.

ስምምነቱም :-

.

ሀማስ በኦክቶበር 7 ድንገተኛ ጥቃት ወቅት አግቶ የት እንዳደረሳቸው ካልታወቁት ከ 200 በላይ እስራኤላዊያን መሃል 50 ዎቹን እንዲለቅ ስምምነቱ የሚያስገድደው ሲሆን

.

በእስራኤል በኩል ደግሞ

.

ለ 4 ቀናት ምንም አይነት ጦርነት እንደማታካሂድና በጋዛና በወረረቻቸው የፍልስጤም ክፍሎች ህጻናትንና አቅመ ደካሞችን ላለመግደል፡፡ እስከስምምነቱ ድረስ አግዳው የነበረዉን አስቸኳይ የምግብና የመድሃኒት ብሎም የነዳጅ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ ተስማምታለች

በጺዮናዊቷ እስራኤል እስር ቤቶች ዉስጥ ከ7200 በላይ ፍልስጤማዊ ያጎረች መሆኑ ይታወቃል

ከነዚህም መሃል እድሜያቸው ከ16 አመት በታች የሆኑ ከ170 በላይ ህጻናት እስረኞችን እንድትለቅ ዉሉ ያስገድዳታል፡፡

ማስታወሻ *** እስራኤል በአለም ላይ ህጻናትን በወታደራዊ ፍርድ ቤት የምትዳኝና እስከ ሃያ አመት ድረስ የምትቀጣ ብቸኛ ሀገር ናት

በእስርቤቶቿ ካጎረቻቸው መሃል ወደ 80 ሴት እስረኞችን በአስቸኳይ እንድለቅ ዉሉ ያስገድዳል

.

በመሰረቱ ይህ ከረጅም የቦምብ ናዳ በኋላ ለደቂቃዎች እንኳን ማግኘት ሳይቻል ቀርቶ የነበረና ለጋዛዊያን የመጣ የ 4 ቀን የእፎይታ የእረፍትና እህል የማግኛ እድል መሆኑ ትልቅ ነገር ነው፡፡

.

በሌላ በኩል ደግሞ ቤተሰቦቻቸው እንደጭራቅና ገዳይ ፣አራጅ ብሎም ርህራሄ የሌለው ሽብርተኛ ተብሎ ሌት ተቀን በእስራኤልና በምዕራባዊያን ሚድያዎች በሚሳለው የሀማስ ቡድን ታፍነዉባቸው የት እንደደረሱ ሳያውቁ በጭንቀት ሌት ተቀን ሲጮሁ ለነበሩ እስራኤላዊያን ቤተሰቦች ቢያንስ ለ 50 ቤተሰቦች ታላቅ የደስታ ብስራት መሆኑ እሙን ነው

.

ያም ሆኖ ስምምነቱ ዘላቂ የተኩስ አቁም ሳይሆን ግዝያዊ ፋታ ነው፡፡ በመሆኑም>

- ከ 4 ቀናት በኋላ ጦርነቱ ዳግም ከተጀመረና ጽዮናዊያኑ ከቶራህ (ብሉይ ኪዳን)1 ኛ ሳሙኤል ቁጥር 5 ትን እያነበነቡና በበለጠ እልህ ጋዛዊያንን እናንተ “ከነ እንስሦቻችሁ ጭምር መጥፋት ያለባችሁ የአማሌክ ህዝቦች” እያሉ ህጻን ሽማግሌ ሳይሉ መግደላቸዉን የሚቀጥሉ ከሆነ

.

- ሀማስ በጉልበቴ አስፈታኋቸው የሚላቸዉንና እስራኤል በዉሉ መሰረት አሁን ተገዳ የምትፈታቸዉን በዛ ያሉ ፍልስጤማዊያን እስረኞች ከእስራኤል መንግስት ተሰዉረው የትም መሄጃ ስለሌላቸው ነገ መልሳ እንደዉም እጥፍ ድርብ አድርጋ የምታስራቸው ወይንም በምታደርገው ወታደራዊ የጅምላ ፍጅት መሃል የምትገድላቸው ከሆነ፣

- ለአለም አቀፍ ህግና ሰብአዊ ድንጋጌዎች ጆሮ የለኝም ያለችው እስራኤል ነገ ተመልሳ ከእርጥባል የሚላኩ የእርዳታ ቀረጢቶችን አላስተናግድም የምትል ከሆነ የዚህ ዉል ፋይዳው ምንድነው ይላሉ?

.

እስኪ ሃሳቦን ያካፍሉ!

.

የቴሌግራም ቻናላችንን ሊንክ ተጭናችሁ ብትገቡ ተጨማሪ መረጃዎችን ታገኛላችሁ

ለተጨማሪ መረጃዎች ከታች ያለዉን የቴለግራም ሊንካችንን ይጫኑ

.

https://t.me/Jemalnuri2

https://t.me/Jemalnuri2

https://t.me/Jemalnuri2

https://t.me/Jemalnuri2

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group