Translation is not possible.

ከላይ የተዘረዘረው ግንዛቤ የዐሊሞቻችን አንዱ ረእይ ማለትም እይታ”dimension” ነው።  በሙሽሪክ እና በአህለል ኪታብ “ኢሥቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለት “ግድባዊ ቃል”Exceptional word” በመሆን ስለ “ዓም” عام ማለትም “ጥቅላዊ መልእክት” እና ስለ “ኻስ” خاص ማለትም “ተናጥሏዊ መልእክት” አይተን ነበር፤ ይህ አንደኛው የዐሊሞቻችን እይታ”dimension” ነው፤ ስለ አህለል ኪታብ ሁለተኛው የዐሊሞቻችን እይታ” ደግሞ “ሢያቅ” سیاق ማለትም “አውዳዊ መልእክት”context” ነው። ይህም ከሙሳ እና ዒሳ ተከታዮች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ ነገር ግን አላህ ከእነርሱም ለእነዚያ ላመኑት ምንዳቸውን ሰጣቸው፤ በእነርሱ ላይ ቁርአን በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፤ እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን» ይላሉ፦

28፥52 እነዚያ ከእርሱ በፊት መጽሐፍን የሰጠናቸው እነርሱ *በእርሱ ያምናሉ*፡፡ الَّذِينَ آتَيْنَاهُمُ الْكِتَابَ مِن قَبْلِهِ هُم بِهِ يُؤْمِنُونَ

28፥53 በእነርሱ ላይ በሚነበብላቸውም ጊዜ «በእርሱ አምነናል፡፡ እርሱ ከጌታችን የኾነ እውነት ነው፡፡ *እኛ ከእርሱ በፊት ሙስሊሞች ነበርን*» ይላሉ፡፡ وَإِذَا يُتْلَىٰ عَلَيْهِمْ قَالُوا آمَنَّا بِهِ إِنَّهُ الْحَقُّ مِن رَّبِّنَا إِنَّا كُنَّا مِن قَبْلِهِ مُسْلِمِينَ

እዚህ ጥቅስ ላይ ልብ አድርግ “እኛ ከእርሱ ማለትም ከቁርአን መውረድ በፊት ሙስሊም ነበርን” ማለታቸው ምክንያታዊ ነው። ሙስሊም” مُسْلِم ትርጉሙ “አቢድ” عَابِدُ ማለትም “አምላኪ” አሊያም “ቃኒት” قَانِتِ ማለትም “ታዛዥ” ማለት ነው። እንደሚታወቀው ከመጽሐፉ ሰዎች ብዙዎቹ አመጸኞች ናቸው፤ አይሁዳውያን አላህ የተቆጣባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳቱተት ናቸው፦

ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3212

ዐዲይ ኢብኑ ሓቲም እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” አሉ፦ አይሁዳውያን የተቆጣባቸው ናቸው፤ ክርስቲያኖች የተሳቱተት ናቸው። عَنْ عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ وَالنَّصَارَى ضُلاَّلٌ ‏”‏ ‏.‏

ነገር ግን ከአይሁዳውያን ጥቂት ያልተቆጣቸው፤ እንዲሁ ከክርስቲያኖች ጥቂት ያልተሳሳቱ ነበሩ፤ እኛም ከመንገዱ እንዳንስት የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋለላቸውን መንገድ ምራን ብለን እንቀራለን፦

1፥7 የእነዚያን በእነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን፣ በእነርሱ ላይ *”ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን”*፤ በሉ። صِرَٰطَ ٱلَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ ٱلْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا ٱلضَّآلِّينَ

ኢማም ቡኻርይ : መጽሐፍ 65, ሐዲስ 4475

አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” አሉ፦ “ኢማሙ፦ “ያልተቆጣህባቸውን እና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ ምራን” ባለ ጊዜ አሚን በሉ፤ عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏”‏ إِذَا قَالَ الإِمَامُ ‏{‏غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلاَ الضَّالِّينَ‏}‏ فَقُولُوا آمِينَ‏.

ስለዚህ ከመጽሐፉ ሰዎች በተውሒድ ያሉትን የኢስራኢል ልጆች እና ነሳራዎች ያረዱትን መብላትን እና በሃላል ሴቶቻቸውን ማግባት ተፈቅዷል፦

5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

“መጽሐፍን የተሰጡት” በሚለው ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ “ሚን” مِنَ ማለትም “ከ” የሚል መስተዋድድ አለ፤ ያ የሚያሳየው ከአህለል ኪታብ መካከል ያሉትን ያላሻረኩ፣ የፍጡር ስም ሳይሆን የአላህን ስም ብቻ የሚጠሩ እና ከዝሙት ብልቶቻቸውን ጥብቆች የሆኑ ሴቶች ማግባት ሙባህ ነው። ይህ ሁለተኛው እይታ ነው። ሁለቱም እይታዎች ቁርኣናዊ ናቸው፤ መርጦ መቀበል የግል ምርጫ ነው።

መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል....

✍ከወንድም ወሒድ ዑመር

https://t.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

Send as a message
Share on my page
Share in the group