Translation is not possible.

“በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ” የሚለው “ዓም” عام ሆኖ ከመጣ በኃላ “የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው” “ኻስ” خاص ሆኖ እንደመጣ ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” ተናግሯል፦

ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 16, ሐዲስ 30

ኢብኑ ዐባሥ”ረ.ዐ” እንደተናገረው፦ 6፥118 “የአላህ ስም በእርሱ ላይ ከተወሳበት እንስሳ ብሉ” የሚለው አንቀጽ እና 6፥116 “በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ” የሚለው አንቀጽ ኢስቲስናዕ በመሆን “የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው” በሚለው ተነሥኻል” عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ، قَالَ ‏{‏ فَكُلُوا مِمَّا ذُكِرَ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ ‏}‏ ‏{‏ وَلاَ تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ ‏}‏ فَنُسِخَ وَاسْتَثْنَى مِنْ ذَلِكَ فَقَالَ ‏{‏ وَطَعَامُ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ حِلٌّ لَكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّ لَهُمْ ‏}‏ ‏.‏

ይህንን ሪዋያህ ሼኹል አልባኒ ሐሠን ነው ብለውቷል፤ “ወኢሥተስና” وَاسْتَثْنَى የሚለው ይሰመርበት፤ “ኢሥቲስናዕ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለት “ግድባዊ ቃል”Exceptional word” ነው፤ ከዚህ ሐዲስ የምረዳው አምላካችን አላህ ከጥቅላዊ መልእክት ተናጥሏዊ መልእክት ይህንን አንቀጽ ማውረዱ ነው፦

5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

አላህ ለሙስሊም ወንድ ከአህለል ኪታብ ሴትን የፈቀደበት ሂክማ ሴት በቀጥታ ሙስሊም ቤት ስለምትገባ ነው፤ በተቃራኒው ሴት ሙስሊም ወንድ ካፊርን ማግባት ያልፈቀደበት ሴቷ ሙስሊም ሙሽሪክ ቤት ስለምትገባ ነው። በማን ስም እንደታረደ ካልታወቀ ደግሞ ቢሥሚላህ ተብሎ መብላት እንደሚቻይ ይህ ሐዲስ ያሳያል፦

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 11

ዓኢሻህ”ረ.ዐ.” እንደተረከችው፦ *”ሕዝቦች፦ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ስጋ በሕዝቦች ለእኛ ቀርቦልናል፤ የአላህ ስም ይወሳበት አይወሳበት እርግጠኛ አይደለንም” አሉ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “የአላህን ስም አውሱበት ከዚያ ብሉት”*። عَنْ عَائِشَةَ ـ رضى الله عنها ـ أَنَّ قَوْمًا، قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ قَوْمًا يَأْتُونَنَا بِاللَّحْمِ لاَ نَدْرِي أَذَكَرُوا اسْمَ اللَّهِ عَلَيْهِ أَمْ لاَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ سَمُّوا اللَّهَ عَلَيْهِ وَكُلُوهُ

የሙሥሊም ስጋ ቤት ካለ አንድ ሙሥሊም ምርጫው መሆን ያለበት የሙሥሊም ስጋ ቤት ነው፤ የሙሥሊም ስጋ ቤት ከሌለ ግን የእነርሱን ስጋ ቤት መጠቀም ሙባህ ነው፦

ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 21, ሐዲስ 17

አቡ ሰለባህ ሲናገር እንደሰማሁት፦ “ወደ አላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሄጄ፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በአህለል ኪታብ አገር ውስጥ ነው የምንኖረው፤ የእነርሱን ምግብ እንበላለን” አልኩኝ፤ እርሳቸውም፦ “ከእነርሱ ሌላ(የሙሥሊም) ካገኘህ ከእነርሱ አትብላ፤ ከእነርሱ ሌላ ካላገኘህ አጥበህ ከእነርሱ ብላ”*። አቡ ዒሣ እንዳለው ይህ ሐዲስ ሐሠን ሰሒሕም ነው። يَقُولُ أَخْبَرَنِي أَبُو إِدْرِيسَ الْخَوْلاَنِيُّ، عَائِذُ اللَّهِ بْنُ عُبَيْدِ اللَّهِ قَالَ سَمِعْتُ أَبَا ثَعْلَبَةَ الْخُشَنِيَّ، يَقُولُ أَتَيْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقُلْتُ يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنَّا بِأَرْضِ قَوْمٍ أَهْلِ كِتَابٍ نَأْكُلُ فِي آنِيَتِهِمْ قَالَ ‏ “‏ إِنْ وَجَدْتُمْ غَيْرَ آنِيَتِهِمْ فَلاَ تَأْكُلُوا فِيهَا فَإِنْ لَمْ تَجِدُوا فَاغْسِلُوهَا وَكُلُوا فِيهَا ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَبُو عِيسَى هَذَا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ

Send as a message
Share on my page
Share in the group