Translation is not possible.

መልስ

5፥5 ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለእናንተ ተፈቀዱ፡፡ *የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ ያረዱት ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለእነሱ የተፈቀደ ነው*፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም *ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው*፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ ٱلْيَوْمَ أُحِلَّ لَكُمُ ٱلطَّيِّبَٰتُ ۖ وَطَعَامُ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ حِلٌّۭ لَّكُمْ وَطَعَامُكُمْ حِلٌّۭ لَّهُمْ ۖ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلْمُؤْمِنَٰتِ وَٱلْمُحْصَنَٰتُ مِنَ ٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْكِتَٰبَ مِن قَبْلِكُمْ إِذَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ أُجُورَهُنَّ مُحْصِنِينَ غَيْرَ مُسَٰفِحِينَ وَلَا مُتَّخِذِىٓ أَخْدَانٍۢ ۗ وَمَن يَكْفُرْ بِٱلْإِيمَٰنِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُۥ وَهُوَ فِى ٱلْـَٔاخِرَةِ مِنَ ٱلْخَٰسِرِينَ

አምላካችን አላህ በእርሱ ላይ ሌሎች ማንነትንና ምንነትን የሚያጋሩ ሙሽሪኮችን እንዳናገባ እና ከእርሱ ስም ውጪ በሌላ ፍጡር ስም ተባርኮ የታረደን እርድ እንዳንበላ ከልክሏል፦

2፥221 *አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው*፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ *ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው*፡፡ ከአጋሪው ጌታ ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው፡፡ *እነዚያ አጋሪዎች ወደ እሳት ይጣራሉ፡፡ አላህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምሕረት ይጠራል*፡፡ ሕግጋቱንም ለሰዎች ይገልጻል እነርሱ ሊገሰጹ ይከጀላልና፡፡ وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ وَلَأَمَةٌ مُّؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ ۗ وَلَا تُنكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ وَلَعَبْدٌ مُّؤْمِنٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ ۗ أُولَـٰئِكَ يَدْعُونَ إِلَى النَّارِ ۖ وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَى الْجَنَّةِ وَالْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِ ۖ وَيُبَيِّنُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ

6፥121 *በእርሱም ላይ የአላህ ስም ካልተጠራበት ነገር አትብሉ*፡፡ እርሱም በእርግጥ አመጽ ነው፡፡ ሰይጣናትም ወደ ወዳጆቻቸው በክትን በመብላት ይከራከሯችሁ ዘንድ ያሾከሹካሉ፡፡ *ብትታዘዙዋቸውም እናንተ በእርግጥ አጋሪዎች ናችሁ*፡፡ وَلَا تَأْكُلُوا مِمَّا لَمْ يُذْكَرِ اسْمُ اللَّهِ عَلَيْهِ وَإِنَّهُ لَفِسْقٌ ۗ وَإِنَّ الشَّيَاطِينَ لَيُوحُونَ إِلَىٰ أَوْلِيَائِهِمْ لِيُجَادِلُوكُمْ ۖ وَإِنْ أَطَعْتُمُوهُمْ إِنَّكُمْ لَمُشْرِكُونَ

“ሺርክ” شِرْك የሚለው ቃል “አሽረከ” أَشْرَكَ ማለትም “አጋራ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ማጋራት” ማለት ነው፤ የሚያጋራው ሰው ደግሞ “ሙሽሪክ” مُشْرِك ማለትም “አጋሪ” ይባላል፤ እንዲሁ በአላህ ላይ የሚያጋሩት ማንነትና ምንነት “ሸሪክ” شَرِيك ማለትም “ተጋሪ” ይባላሉ፤ ከአህለል ኪታብ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም ከነሳራዎች አበይት የሚባሉት ሙሽሪኪን ናቸው፦

5፤72 *እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ*፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» *እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በእርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ*፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡ لَقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ ۖ وَقَالَ الْمَسِيحُ يَا بَنِي إِسْرَائِيلَ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ ۖ إِنَّهُ مَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدْ حَرَّمَ اللَّهُ عَلَيْهِ الْجَنَّةَ وَمَأْوَاهُ النَّارُ ۖ وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ أَنصَارٍ

እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፤ እነሆ ይህ ንግግራቸው ማጋራት ነውና አላህ በእርሱ ላይ የሚያጋራ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፤ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ይህ ጥቅላዊ መልእክት “ሙጅመል” مجمل ወይም “ዓም” عام ይባላል፤ ነገር ግን አላህ ከሙሽሪኪን አህለል ኪታቦችን በተናጥል “ሙፈሰል” مُفَصَّل ወይም “ኻስ” خاص በማድረግ ለያቸው፤ ይህም ሙሽሪኪን እና አህለል ኪታብ በሚሉ ቃላት መካከል “ወ” وَ ማለትም “እና” የሚል መስተጻምር አስቀምጧል፦

98፥1 *እነዚያ ከመጽሐፉ ባለቤቶች እና ከአጋሪዎቹም የካዱት ግልጹ አስረጅ እስከ መጣላቸው ድረስ ተወጋጆች አልነበሩም፡፡ لَمْ يَكُنِ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ أَهْلِ الْكِتَابِ وَالْمُشْرِكِينَ مُنفَكِّينَ حَتَّىٰ تَأْتِيَهُمُ الْبَيِّنَةُ

Send as a message
Share on my page
Share in the group