لا يمكن الترجمة

🔵 ዲን ምክክር (አደራ መባባል ) ነዉ !

يقول ﷺ: الدين النصيحة قلنا: لمن يا رسول الله؟ قال: لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم. فهذا الحديث العظيم يدل على أن الدين هو النصيحة، وذلك

የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

ዲን መመካከር አደራ መባባል ነዉ አሉ ሶሀባዎችም የአላህ መልክተኛ ሆን ዲን መመካከር ነዉ ሲባል ለማን አሉ መልክተኛዉም ለአላህ:ለቁርአን :ለመልክተኛዉ :ለሙስሊም መሪዎችና ለኡለማዎች እና አጠቃላይ ለሙስሊሙ ማህበረ ሰብ ነዉ አሉት

👉በዚህ ሀዲስ መልክተኛዉ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ዲን ላይ መመካከር ግዴታና አስፈላጊ መሆኑ አስረግጠዉ ነግረዉናል

♦️ለማን ነዉ የምንመካከረዉ ?

👉ለአላህ አላህ በመፍጠር ብቸኛ መሆኑ

ለአላህ ስምና ባህሪያት በዚህ ላይ ብልሹ አካሄድ የሚሄዱ የጥመት አንጃዎች ሊመክር ይገባል ።

አምልኮ ለአላህ  ብቻ በማረግ ላይ መመካከር

👉ለቁርአን ቁርአን በትክክል እየቀራን ነዉ እያስቀራን ነዉ ሒወታችን በቁርአን እያኖርን ነዉ እራሳችን እንፈትሽ በዚህ ላይ መመካከር

👉ለመልክተኛዉ መመካከር ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀቃቸዉን መጠበቅ ክብራቸዉን ማወቅ ለክብራቸዉ ዘብ መሆን ሰዉ መሆናቸዉ ማወቅ ቤተሰቦቻችሁ ሶሀባዎቻቸዉ ማክበር

👉ለመሪዎችን መሪዎችን መተመለከተ የሚኖር መመካከር

የሙስሊም መሪዎች ችግሮች ክፍተቶች ሊኖር ይችላል ይኖራልም ከዚህም ጋር መሪነታቸዉን አምኖ መቀበል መልካም ስራዎቻቸዉን ማሰራጨት ክፉ ነገራቸዉን ያዝ ማረግ መምከር የሚያስፈልግ ከሆነ ፊትና በማይቀሰቅስ መልኩ ደበቅ አርጎ መምከር ካልሆነ ሰላም አይኖርም ደም ይፋሰሳልና አገር ይወድማል  በዚህ ዘመን ግን ብዙዎች የሙስሊም መሪዎች ማብጠልጠል ማንቋሸሽ ላይ ተጠምደዋል ይህ አካሄድ ከመልክተኛዉ አስተምሮ ጋር ይጋጫል ይህ ባለስልጣንን የሚመለከት ነዉ።

ኡለማዎች በተመለከተ ኡለማዎችን መዉደድ:የኡለማዎች ክብር የሚያጎድፍ የሚያጣጥል የሆነ አካል የራሱን ሀይማኖት እያጣጣለ ነዉ ።እነሱን ማክበር ከጎናቸዉ በመሆን አቅማችን በፈቀደ መልኩ ማገዝ በአጭሩ ትክክለኛ የሱና  ኡለማዎችን መዉደድ ዲንን ከመዉደድ ነዉ ኡለማዎችን መጥላት ዲንን ከመጥላት ይመደባል

👉ስለህዝበ ሙስሊሙ መመካከር ሲባል ለዱንያዉም ይሁን ለአኼራዉ የሚጎዳዉን ነገር እያዩ አለማለፍ ወደተሻለዉ መንገድ ማመላከት ከመጥፎ መከላከል ከጥሩ ማዘዝ በተለይም

ተዉሒድን አስቀድሞ ከቢዳአም ከሽርክም አስጠንቅቆ እዉነተኛ የሆነዉን መቆርቆርን ማስገኘት

🔹ሀዲሱ ጠቅለል ስናረገዉ ዲን ምክክር ነዉ ብለዉ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጠቅለል አርገዉ መግለጻቸዉ መመካከር ትልቅ ደረጃ እንዳለዉ ለማሳየት ነዉ ።

መመካከር ሲባል እያንዳንዱ ሼህ ዳኢ ኡስታዝ

እሰከሚሆን መጠበቅ የለበትም

ለወንድሙ  :ለእህቱ :ለአባቱ ለእናቱ ለቤተሰቡ ለጓደኛዉ  ወዘተ አላህ ባገራል ልክ ቴክኖሎጂዉን በመጠቀም ተቆርቋሪነታችን ማሳየት አለበት ለዱንያ ለአሄራ ከሚጎዳቸዉ ነገር ወደሚጠቅማቸዉ ነገር መጣራት አለበት

🔹ሌላዉ ከሀዲሱ የምንወስደዉ የመካከር ዘርፎች የታወቁ መሆኑ

ለአላህ

ለቁርአን

ለመልክተኛዉ

ለኡለሞችና ለሙስላም መሪዎች

ለህዝበ ሙስሊሙ ናቸዉ

ጠዋት ማታ ለቤተሰብ የምንቆረዉ በጠላት እንዳይደፈሩ እንዳይራቡ ነዉ ዋናዉ ግን ለአሄራቸዉ የሚጠቅማቸዉ ላይ ልንለፋ ይገባል

🔹መመካከር ዲን ከሆነ የዚህ ተቃራኒ ማጭበርበር መሸወድ መንገድ ማሳት የዲን ተቃራኒ ነዉ ስለአላህ ከመመካከር ተቃራኒ አቅጣጫ እንዲስቱ ማረግ

ከኡስታዝ ኢብኑ ምነዉር ደርስ ተቀንጭቦ የተወሰደ ተጻፈ በአቡ አብዱራህማን

https://t.me/Rremedan

Telegram: Contact @Rremedan

Telegram: Contact @Rremedan

አንዳንዴ የባጢል ሰዎች ወይም ቡድኖች የምናጋልጥበትና የተለያዩ ሙሀደራዎች፣ ደርሶች፣ አስተማሪ ጹሁፎች የሚተላለፍበት ቻናል
أرسل كرسالة
شارك على صفحتي
شارك في المجموعة