Translation is not possible.

ሸሪዓው ወንዶች ልብሳቸውን ሱሪያቸውን፣ጀለብያቸውን፣ሽርጣቸውን ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ ታዘዋል።

ሴቶች ደግሞ መላ ሰውነታቸውን በሒጃብ እንዲሸፍኑ፣ ስስ ያልሆነ የሰውነታቸውን ቅርፅ የማያሳይ፣ የሆነና ከቁርጭምጭሚት በታች አንድ ስንዝር ለቀቅ አድርገው እንዲለብሱ ታዘዋል።

የሚገርመው በአሁን ሰዓት አንዳንዶች ዘንድ ነገሩ በተቃራኒ ሆኗል።

ወንዶች ልብሳቸውን አሳጥረው ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው እንዲለብሱ ታዘው ሳለ እንደ ሴቶች ካለበስን መሬት እየጎተትን መሬት ካልጠረግን አሉ።

ሴቶች ደግሞ በተቃራኒው ከቁርጭምጭሚት ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ የታዘዙት እነሱ ይመስል ከቁርጭምጭሚት ከፍ አድርገው ያውም ስስ የሆነ ያውም በጣም ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ የሰውነታቸውን ቅርፅ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ካለበስን አሉ።

በጣም የሚገርመው ከወንዶችም ከሴቶች ወደ ሰላት ሲገቡ ወንዱም ሱሪውን ወደ ላይ ያጥፈዋል።ሴቷም የለበሰችውን ቀሚሷን ወደ ታች ዝቅ ለማድረግ ትሞክራለች።

ስለዚህ ሸሪዓው ያዘዘውን አለባበስ ምን አይነት አለባበስ እንደሆነ ያውቃሉ ማለት ነው። ሸሪዓው ወንዶችን ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገው አሳጥረው እንዲለብሱ የታዘዙት በሰላት ብቻ አይደለም። በየትኛውም ሁኔታ ነው። ሴቷም እንዲሁ በሰላት ብቻ አይደለም መላ ሰውነቷን እንድትሸፍን የታዘዘችው። ይህን ያልኩት ከላይ እንዳልኳችሁ ወንዱም ልክ ወደ ሰላት ሊገባ ሲል ሱሪውን ወደ ላይ ለማጠፍ ሲሞክር ታየዋለህ። ሴቷም ልብሷን ወደ ታች ዝቅ ለማድረግ ትሞክራለች።

ወንድሜ ሆይ! ሱሪህን፣ጀለብያህን፣ሽርጥህን ሸሪዓው ባዘዘው መልኩ ከቁርጭምጭሚት በላይ ከፍ አድርገህ አሳጥረህ ልበስ። አርኣያዎችህ እነ አቡበክር፣እነ ዑመር፣እነ ዑስማን፣እነ ዐሊይና የመሳሰሉት ናቸው። ዑመር በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ሊዘይሩት ከመጡ ሰዎች መካከል አንድ ወጣት ሱሪውን ሲጎትት ተመለከተው  አስጠርቶ በዚህ ሁኔታ ላይ ሆኖ ምንድነው ያለው አንተ ልጅ ሆይ ልብስህን ከፍ አድርገህ ልበስ። ይህ ለልብስህ ንፅህና የተሻለ ነው። ጌታህንም ለመፍራት የቀረበ ነው ብሎ ነው የመከረው። ዑመር በሞት አፋፍ ላይ ሆኖ ይህን ማለቱ ጉዳዩ በጣም ከባድ መሆኑን ነው የሚያሳየው።

እህቴ ሆይ! አንቺም አርኣያዎችሽ እነ ዓኢሻ፣እነ ኸዲጃ፣እነ ሱመያ፣እነ ሐፍሳና የመሳሰሉት ናቸው። እነሱን ተከተይ።

በነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘመን ያቺ አዙሮ የምጥል በሽታ የነበረባትን ሴት ተመልከቺ። በሽታው በጣም ያሰቃያት ነበርና በሽታው አዙሮ ሲጥላት ሰውነቷ ይገላለጣል።ይህቺ ሴት ለነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ምንድነው ያለችው እኔ የሚጥል በሽታ አለብኝ። በምወድቅበት ሰዓት ሰውነቴ ይገለጣል። ምን ላድርግ ብላ ስትጠይቃቸው የአላህ መልዕክተኛ ምንድነው ያሏት ከፈለግሽ አላህ ይህን በሽታ እንዲያነሳልሽ ዱዓ አደርግልሻለሁ። ከፈለግሽ ሰብር አድርጊ ጀነት አለልሽ አሏት። የሷ ምላሽ ምን ነበር ሰብር አደርጋለሁ። በሽታው በሚጥለኝ ሰዓት ሰውነቴ እንዳይገላለጥ ዱዓ አድርጉልኝ ነበር። ታዲያ አንቺና ይህቺ  በበሽታ ምክንያት ራሷን ስታ በምትወድቅበት ሰውነቷ ለሚገላለጠው የሚትጨነቅ ሴት የትና የት ናችሁ?

      🖌ወንድማችሁ አቡ መርየም

Send as a message
Share on my page
Share in the group