የነፃነትና እኩልነት ብሔራዊ ምክርቤት "ነእፓ በ5ኛ አመት ዋዜማ ላይ" በሚል መሪ ቃል ከሕዳር 8/2016 እስከ ሕዳር 9/2016 ያካሄደው 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ በስኬት አጠናቀቀ።
(አዲስአበባ ፤ ህዳር 10/2016 ዓ/ም)
ስብሰባውን በንግግር የከፈቱት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ዓብዱልቃድር አደም ሲሆኑ ሊቀመንበሩ ለምክርቤቱ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ነእፓ በ5ተኛ አመት ዋዜማ ላይ የሚገኝ መሆኑን በማስተዋስ ፓርቲው ከተፎካካሪነት ወደ መሪነት ለሚያደርገው ግስጋሴ ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ቁመና እንደሚገኝ ገልጸዋል። በመቀጠል ሊቀመንበሩ የስብሰባው ዋና ዓላማ በ2015ዓ.ም ዕቅድ ክንውን፣ በውጭ አዲት ሪፖርተር የተዘጋጀ የኦዲትሪፖርት፣ ለ2016 የተዘጋጀው የፓርቲው ዕቅድ፣ የፓርቲው ስትራቴጂክ እቅድ መገምግገም እና ማጽደቅ እንዲሁም ፓርቲው ያዘጋጃቸው ሶስት ወሳኝ ሰነዶች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ መሆኑን አቅጣጫ በመስጠት የውይይት መድረኩን አስጀምረዋል፡፡
ቅዳሜ በነበረው ስብሰባ ምክርቤቱ መጀመሪያ የ2015ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀምና የፓርቲው የ2015 በውጭ ኦዲተር የተረጋገጠ የሒሳብ ሪፖርት በመገምገም አጽድቋል። ምክርቤቱ ፓርቲው በ2015 ፓርቲው ጥሩ እንቅስቃሴ እና ውጤት እንዳሳየ ገምግሟል።በመቀጠል ምክርቤቱ የፓርቲው የአምስት ስትራቴጂክ እቅድ እና የ2016ዓ.ም ዕቅድ ዝግጅት ቀርቦለት ተወያይቶ አጽድቋል። ምክርቤቱ ቅዳሜ በነበረው ውሎ ካጽደቃቸው ወሳኝ አጀንዳዎች መካከል የፓርቲው የፖለቲካ አካዳሚ ማቋቋሚያ ደንብ ነው።
እሁድ (ሕዳር 9/2019) ቀጥሎ በዋለው ስብሰባ ላይ ምክርቤቱ በሁለት አበይት ጉዳዮች የተወያየ ሲሆን መጀመሪአያ ፓርቲው ባሰናዳው የአገራዊ ምክክር ሰነድ ላይ ዘለግ ያለ ውይይት በማድረግ ሰነዱን በሙሉ ድምጽ አጽድቆ አሳልፎታል። በመቀጠል ምክርቤቱ የፓርቲው ፖለቲካ አካዳሚ ማቋቋሚያ ደንብ መርምሮ አጽድቋል።
ከላይ ከተጠቀሱት አበይት ክንዋኔዎች በተጨማሪ የምክርቤቱ አባላት በemotional intelligence ዙሪያ አጭር ስልጠና ወስደዋል።
ነእፓ :- ህዝብ ግንኙነት