Translation is not possible.

#የነፍስ_ወግ

በሁለተኛው ኸሊፋ በዑመር (ረድየላሁ ዐንሁ) ዘመን ሶስት ወጣቶች አንድ ሰውዬን ጎትተው በማምጣት ‹‹ያዐሚረል ሙእሚኒን (የሙስሊሞች መሪ ሆይ) ይህ ሰው አባታችንን ገድሏል ቅጣት እንድትወስንበት እንሻለን›› በማለት በእልህና በቁጣ ተናገሩ፡፡

‹‹ለምን ገደልክ?›› ሲል ዑመር ረጋ ብለው ጠየቁ።

‹‹እኔ የግመል እረኛ ነኝ። አንደኛው ግመሌ የአባታቸው መሬት ላይ ካለ ዛፍ ቅጠል ቀንጥሶ ሲበላ አባታቸው ድንጋይ ወርውሮ ሲመታው ግመሌ ሞተ እኔም እሱ የወረወረውን ድንጋይ አንስቼ ስወረውር መታሁትና ሞተ›› ሲል ተናገረ፡፡

‹‹እንደዛ ከሆነ ቅጣት እወስንብሃለሁ!›› አሉ ዑመር (ረድየላሁ ዐንሁ)::

‹‹እሺ ሦስት ቀናትን አቆየኝ። ምክንያቱም አባቴ ሲሞት ለእኔ እና ለወንድሞቼ የተወው ከንዝ/የተደበቀ ሃብት/አለ እኔ አሁን እዚሁ ከሞትኩ ከንዙም ይጠፋል ወንድሞቼም ይጠፋሉ(ይቸገራሉ)። ስለዚህ ልሂድ ፍቀድልኝና ተመልሼ እመጣለሁ›› አለ ተከሳሹ፡፡

‹‹ታዲያ እሰክትመለስ ዋስ የሚሆንህ ማነው?›› በማለት ዑመር (ረድየላሁ ዐንሁ) ጠየቁ።

ሰውዬው የተሰበሰቡትን ሰዎች ተመለከተ የሚያውቀው የለም። ደጋግሞ የእያነዳንዳቸውን ፊት ተመለከተና

‹‹ያ ሰውዬ እዛ ጋ የቆመው ›› በማለት ከመካከላቸው አንዱን ጠቆመ።

‹‹ያ አባ ዘር ለዚህ ሰው ዋስ ትሆናለህ?›› በማለት ዑመር (ረድየላሁ ዐንሁ) የተጠቆመውን ሰው ጠየቀው።

‹‹አዎን ያ አሚረል ሙእሚኒን›› በማለት መለሰ::

‹‹ይህ ሰው ካመለጠ ቅጣቱ አንተ ላይ ተፈፃሚ እንደሚሆን አታውቅም እንዴ? ›› ሲል ዑመር ተገርሞ ጠየቀ።

‹‹ግድ የለም ያ አሚረል ሙእሚኒን እኔ ዋስ እሆነዋለሁ።›› ሲል አቡዘር መለሰ፤ ሰውየው ሄደ፡፡

አንድ ቀን አለፈ….ሁለተኛው ቀን ተከተለ…በሦስተኛው ቀን ….ሰውየው ካልመጣ ቅጣቱ አቡዘር ላይ ስለሚፈፀም ሰዎች ተጨነቁ። ሆኖም በሶስተኛው ቀን ከመግሪብ (ከመምሸቱ በፊት ) በፊት …..ያ ሰው እያለከለከ መጣ። በጣም እንደደከመው ገፅታው መስካሪ ነበር፡፡ ከዑመር (ረድየላሁ ዐንሁ) ፊት ለፊት መጥቶ በመቆም

‹‹የውርስ ሀብቱን ለወንድሞቼ እና ለእናቴ ወንድሞች አስረክቤ መጣሁ። አሁን በቁጥጥርህ ስር ሆኛለሁ ቅጣቱን ፈፅምብኝ›› በማለት ተናገረ፡፡

ዑመር (ረድየላሁ ዐንሁ) ተገረሙ። ‹‹በዚያው ማምለጥ የምትችል ሆነህ እንዴት ተመለስክ?›› ሲሉ ጠየቁት፡፡

‹‹ሰዎች ዘንድ ‹ቃል አክባሪነት ጠፋ› እንዳይባል ፈርቼ ነው›› በማለት መለሰ ተከሳሹ ፡፡

ዑመር ወደ አቡዘር (ወደተዋሰው ሰው ) ዙረው ‹‹ይህን ሰው እንዴት ዋስ ሆንከው? ›› በማለት ጠየቁ።

‹‹እኔማ ዋስ የሆነኩት በሰዎች ዘንድ ኸይር/መልካም/ ስራ ጠፋ እንዳይባል ፈርቼ ነው››ሲል አቡ ዘር (ረድየላሁ ዐንሁ) መለሱ፡፡

በሁኔታው የሟች ልጆች ልብ ተነካ። ‹‹በቃ አፉ ብለነዋል (ምረነዋል )። ቅጣቱ እንዳይፈፀምበት›› ሲሉ ተናገሩ።

ዑመር (ረድየላሁ ዐንሁ) ‹‹ለምን?›› ሲል ጠየቃቸው።

‹‹እኛ ደግሞ በሰዎች መሃል ‹ይቅር መባባል ጠፋ› እንዳይባል እንፈራለን›› አሉ።

——————

የውሳኔህን እና የድርጊትህን ተጽእኖ ስትረዳ ምግባርህንም ትገራለህ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group