Translation is not possible.

አላህ ንግዳችሁን አትራፊ አያድርገው

~

ባንኮች ከመስጂድ ግቢ ውስጥ እንዲህ ዓይነት ስራ ሲሰሩ ዝም ብሎ ማየት አይገባም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

إِذَا رَأَيْتُمْ مَنْ يَبِيعُ أَوْ يَبْتَاعُ فِي الْمَسْجِدِ فَقُولُوا : لَا أَرْبَحَ اللَّهُ تِجَارَتَكَ

{መስጂድ ውስጥ የሚሸጥ ወይም የሚገዛ ካያችሁ 'አላህ ንግድህን አያትርፍልህ' በሉት።" [አልኢርዋእ፡ 1295]

ለእንዲህ አይነት ጥፋት ተጠያቂዎቹ የመስጂድ ኮሚቴዎች፣ ሙስሊም የሆኑ የባንክ ሰራተኞች፣ የባንኮቹ "የሸሪዐ" አማካሪዎች ናቸው። ሁላችሁም አላህን ፍሩ። መስጂዶች የአምልኮት ቦታዎች እንጂ የቢዝነስ ማእከላት አይደሉም።

እኛ ደግሞ ጉዳዩን ለኮሚቴ ብቻ ልንተው አይገባም። መስጂዶችኮ የኮሚቴዎች የግል ንብረቶች አይደሉም። መስጂዶች የአላህ ቤቶች፣ የሁሉም ሙስሊም መገልገያዎች እንጂ የማንም የግል ሁዳድ አይደሉም። በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል ሁላችንንም ይመለከታል። ስለዚህ ሃይማኖታችን የማይፈቅዳቸው ተግባራት ሲፈፀሙባቸው ስናይ ምናገባኝ ልንል፣ ዝም ብለን ልናልፍ አይገባም። ሁከት በማይፈጥር መልኩ እንዲወጡ ልናደርግ ይገባል።

=

✍️Ibnu Munewor

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group