Translation is not possible.

ከጠየቅኩት በላይ ሰጥቶኛል፣ ከጥረቴ በላይ ሸልሞኛል፣ ከለመንኩት በላይ ለግሶኛል። ርቄው አልተወኝም፣ ሸሽቼው አልጣለኝም፣ ረስቼዉም አልረሳኝም። ካሰብኩት በላይ አድርጎልኛል ፣ አይታሰብም ያልኩትን አሳክቶልኛል፣ ጥፋቴን እያየ አልፎኛል፣ ዉርደቴን እያወቀ ሰትሮኛል፣ ለኔ በማይገባኝ መልኩ ተንከባክቦኛል፣ ጠብቆኛል፣  በዙርያዬ ባሉት ዘንድ አሳምሮኛል። ሥሜን ጠብቆልኛል።

እዝነቱና ችሮታው ባይኖርልኝ ኖሮ መቸ ቆሜ እሄድ ነበር።

አላህ ሆይ! በሁሉም ሁኔታዬ ዉስጥ ምስጋና ላንተ ይሁን። በመሸ በነጋ ቁጥር ሥምህ ዘወትር ከፍ ይበል

Send as a message
Share on my page
Share in the group