Translation is not possible.

የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲን በተለያየ መንገድ የማጠልሸት ሴራ

;;;;;;;;;;;;;;;;;      ;;;;;;;;;;;;;;

እኔ የሚገርመኝ ሁል ጊዜ አል-ኢኽዋን አል-ሙስሊሚን ሳዑዲን ለማጠልሸት የሚጥሩበትን መንገድ እንደየ ቦታው መለያየታቸው ነው።

ሸሪዓን ለሚወደውና ለሚደግፈው ለሙስሊሙ የህብረተሰብ ክፍል ልክ ለዲኑ እንደተቆረቆረ፣ ሳዑዲ ሸሪዓን ጥሳ እንዲህ አደረገች፣ እንዲህ አደረገች፣ በቃ እኮ አሁንማ ተበላሸች፣ አለቀላት፣ ዓሊሞችን ማሰር ጀመረች፣ በአውሮፓዎች ቀኝ አገዛዝ ወደቀች… ወዘተ እያሉ ያታልሉታል።

አውሮፓዎች ጋር ሲሄዱ ደግሞ ሳዑዲ አንባገነን ናት፣ ዲሞክራሲን አታከብርም፣ ሴቶችን አፍናለች፣ በነፃነት መናገር የለም… የመሳሰሉትን እያሉ ሳዑዲ ላይ ያነሳሱዋቸዋል። ምን ይሄ ብቻ ለግብረ-ሰዶማውያን መብትም ይከራከራሉ። ሁልጊዜም ትግላቸው ሳዑዲን እንደ ቱኒዚያ፣ሶሪያ፣ግብፅና ሊቢያ… ለማውደም ነው። እኔን ይበልጥ የሚገርመኝ ደግሞ እዚሁ ቁጭ ብሎ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሳዑዲን እንዲጠላ የሚያራግቡ የነ ሰልማነል አውዳ ቡችሎች ናቸው!።

ውስጧ ያሉት ኢኽዋኖች ከውጮች አይሻሉም፣ ውጪ ያሉት ከውስጦች አይሻሉም፣ ሆኖም ግን አላህ በረህመቱ ከሺዓም፣ ከአይሁድም፣ ከኢኽዋንም፣ ተንኮልና ሴራ ጠብቋታል!። ኢንሻአላህ ወደፊትም ይጠብቃታል!!።

አመራሮች ላይ ችግሮች የሉም ፍፁም ናቸው ማለቴ እንዳልሆነ ይሰመርበት!፣ ነገር ግን እንደ ኢስላም ሙስሊሙ ህብረተሰብ መሪውን ሲሳሳት በዓሊሞቹ መምከር ማስመከር ነው እንጂ፣ እየተቹ ከተቻለ ለጠላት አሳልፎ መስጠት፣ ይህ ካልተሳካም የእርስበርስ ጦርነት ቀስቅሶ የሙስሊሙን ደም ማፋሰስና ሸሪዓዊ ነገሮች እንዲወድሙ ማድረግ የዘመናዊ ኸዋሪጆች የኢኽዋኖች ልዩ መገለጫ እንጂ ፈፅሞ ሸሪዓው ያስቀመጠው የሙስሊሞች ስርኣት አይደለም!።

እኔ ሙስሊሙን ህብረተሰብ አደራ የምለው ነገር ቢኖር፣ የተውሒዷን ሀገር ሳዑዲንና ዓሊሞቿን አላህ እንዲጠብቅ፣ መሪዎቿን ሲሳሳቱ አላህ እንዲያስተካክላቸው ከልብ ዱዓ እንዲያደርግ ነው።

✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ

https://telegram.me/IbnShifa

https://telegram.me/IbnShifa

Send as a message
Share on my page
Share in the group