Tarjima qilib boʻlmadi.

➭የፊደላት መውጫ ቦታ 17 ሲሆን ዋና ዋናዎቹ 5 ናቸው።

እነሱም ፦1⃣ ጀውፍ

2⃣ ሀልቅ

3⃣ ሊሳን

4⃣ ሸፈታን

5⃣ ኸይሹም

1⃣ አል-ጀውፍ*/

✔ጀውፍ ማለት በቋንቋ ደረጃ ባዶ ቦታ ማለት ሲሆን በተጅዊድ ሙሁራን ገለፃ ደግሞ የአፍና የጉሮሮ ባዶ ቦታ ማለት ነው።

➛ በዚህ ቦታ ሶስቱ የመሳቢያ ፊደሎች ይወጣሉ። እነሱም፦

1اስኩን

2وስኩን

3يስኩን

እነዚህ ሀርፎች መደል አስሊ ወይም መደል ጠብዒ በመባል ይታወቃሉ።መደል ጠብዒ ለመባል የሚከተሉትን መስፈርት ማሟላት አለባቸው።

1✅አሊፍ(ا) ስኩን ሆኖ ቀድሞት የመጣው ሀርፍ ፈትሀ መሆን አለበት።

2✅ዋው(و)ስኩን ሆኖ ቀድሞት የመጣው ሀርፍ ዶማ መሆን አለበት።

3✅ያ(ي)ስኩን ሆኖ ቀድሞት የመጣው ሀርፍ ከስራ መሆን አለበት።በዚህ መልኩ ስናገኛቸው የሁለት ሀረካ ያክል እንስባቸዋለን።

በሉ ገመጥ እያረጋችሁ

*2⃣አል-ሀልቅ*/

✔ሀልቅ ማለት ጉሮሮ ማለት ሲሆን ይህ ቦታ በ3ይከፈላል።

➛ከያንዳንዱ መውጫ ቦታ ደግሞሁለት ሁለት ሀርፎች ይወጣሉ።

1✅አቅሰል ሀልቅ(ከልብ ከፍ ብሎ ለአፍ እሩቅ የሆነው) ሲሆን ከዚህ ቦታ ሁለት ሀርፎች ይወጣሉ።

1ሀምዛ (ء)

2ሀ(ه)መርቡጣ ይወጣሉ።

2✅ወሰጠል ሀልቅ(የጉሮሮ መካከለኛው ክፍል) ሲሆን ከዚህም ቦታ ሁለት ሀርፎች ይወጣሉ።

1ልሟ ሀ(ح)

2ዐይን(ع) ይወጣሉ።

3⃣አድነል ሀልቅ( ለአፍ ቅርብ የሆነ የጉሮሮ ክፍል ሲሆን ከዚህም ቦታ ሁለት ሀርፎች ይወጣሉ።

1ኸ(خ)

2ገይን(غ) ይወጣሉ።

በሉ እየጠጣችሁ ጉሮሯችሁን አለስልሱ።እቀጥል

*3 አል-ሊሳን*/

✔ሊሳን ማለት ምላስ ማለት ሲሆን በውስጡ 10 መውጫ ቦታዎች አሉት።በነዚህም መውጫ ቦታዎች 18 ሀርፎች ይወጣሉ።

➛ይህ ቦታ ደግሞ አራት ዋና ዋና መውጫ ቦታ አለው።እነሱም፦

1✅አቅሶል ሊሳን

2✅ወሰጠል ሊሳን

3✅ሀፈቱል ሊሳን

4✅ጠረፈል ሊሳን

1✅አቅሶል ሊሳን ማለት የምላስ መጨረሻው ክፍል ማለት ሲሆን ይህ ቦታ ሁለት መውጫ በር አለው።

1የካፍ(ك)መውጫ በር ሲሆን

2የቃፍ(ق)መውጫ በር ነው።

➛እዚህ ላይ ሁለት መውጫ ቦታ ና ሁለት ሀርፍ አገኘን ማለት ነው።

2✅ወሰጦል ሊሳን ማለት የምላስ መካከለኛው ክፍል ማለት ሲሆን ይህ ቦታ አንድ በር አለው በዚህ በር 3ሀርፎች ተከባብረው ይወጣሉ።እነሱም፦

1ጂም(ج)

2ሺን(ش)

3ያ(ي)ከመድ ሀርፍ ውጭ የሆነችው ወይም የተሀረከችው።

➛ከዚህ ቦታ ደግሞ አንድ መውጫ እና ሶስት ሀርፎች አገኘን ማለት ነው።

3✅ሀፈቱል ሊሳን ማለት የምላስ ጎን ማለት ሲሆን ይህ ቦታ ሁለት መውጫ በር አለው።

1የዷድ(ض)በር ሲሆን

2የላም(ل)በር ነው።

➛ከዚህ ቦታ ደግሞ ሁለት መውጫ ቦታ ና ሁለት ሀርፎች አገኘን ማለት ነው።እስካሁን አምስት በር እና ሰባት ሀርፍ አገኘን ማለት ነው።

እቀጥል አራተኛው ና የመጨረሻው የምላስ ክፍል

4✅ጠረፈል ሊሳን ማለት የምላስ ጫፍ ማለት ሲሆን ከዚህም ቦታ አምስት መውጫ በር እና አስራአንድ ሀርፎች እናገኛለን።

1የኑን መውጫ(ن)

2የሯ መውጫ(ر)

3የጧ(ط)

የዳል(د) ና

የታእ(ت) መውጫ

4 የሷድ(ص)

የሲን(س) ና

የዛ(ز)

5 የዟ(ظ)

የዛል(ذ)

የሣእ(ث)

➛በዚህ መልኩ 10 መውጫ ቦታ ና 18 ሀርፎች አገኘን ማለት ነው።እሽ እስኪ አረፍ በሉና ምግብ ቅመሱ ከዛ ደግሞ እንቀጥላለን በዛውም ያልገባንን በወረቀት እንፃፍ እና እንጠይቅ።

*4⃣ አል-ሸፈታን*/

✔ሸፈታን ማለት ሁለት ከንፈሮች ማለት ሲሆን ሁለት መውጫ ቦታዎች እና አምስት ሀርፎችን እናገኛለን።

እነሱም፦1 የፋ(ف)መውጫ ቦታ

2 የዋው(و)

የሚም(م)

የባ(ب) መውጫ ቦታ

*5⃣ አል ኸይሹም*/

✔ኸይሹም ማለት ኮሽኮሾ ወይም የአፍንጫ ሩቅ ክፍል ከውስጠኛው የአፍ ክፍል ጋር የሚያገናኘው የአፍንጫ ቀዳዳው ክፍል ማለት ነው።

ይህ ቦታ አንድ መውጫ ሲኖረው ከዚህም ቦታ ጉና ይወጣል።

✅ጉና ማለት ደግሞ ዜማ ይባላል።በአብዛሀኛው ግዜ ኑን ሸዳ እና ሚም ሸዳ ላይ ይገኛል።

እሽ እህቶች እንዴት ነው ግልፅ ነው እየተግባባን ነው።

እስኪ ወደ ኋላ መለስ እንበል መጀመሪያ ላይ የፊደላት መውጫ ቦታ 17 እንደሆኑ አይተናል።ዋና ዋናዎቹ ደግሞ አምስት እንደሆኑ አይተናል እስኪ አብረን እንቁጠር።17ቱን

*1➛አሊፍ ا ስኩን፣ዋው و ስኩን እና ያ ي ስኩን መውጫ ቦታ*/

*2➛የሀምዛ ء እና የሀ መርቡጣه መውጫ ቦታ*/

*3➛የልሟ ሀ ح እና የዐይን ع መውጫ*/

*4➛የኸ خ እና የገይን غ መውጫ*

*5➛የቃፍ ق መውጫ*

*6➛የካፍ ك መውጫ*

*7➛የያ ي ፣የሺን ش እና የጂም ج መውጫ*

*8➛የዷድ ض መውጫ*

*9➛የላም ل መውጫ*

*10➛የኑን ن መውጫ*

*11➛የሯ ر መውጫ*

*12➛የታ ت ፣የዳል د እና የጧ ط መውጫ*

*13➛የሲን س ፣የዛ ز እና የሷድ ص መውጫ*

*14➛የሣ ث ፣የዛል ذ እና የዟ ز መውጫ*

*15➛የፋ ف መውጫ*

*16➛የዋውو ፣የባ ب እና የሚም م መውጫ*

*17➛ጉና ይባላል።*

ይህን ይመስላል እንግዲህ 17 መውጫ እና 31 ሀርፎች

image
image
image
image
image
image
image
Xabar sifatida yuborish
Sahifamda baham ko'rish
Guruhda ulashish