Translation is not possible.

ተዉበት ሳታረግ ብትሞትስ ?

- አንድ አል-አዕሻ የተባለ ሰዉ ነበረ ይባላል። ይህ ሰዉ እስልምናን ለመቀበል ወደ መዲን በመሄድ ላይ ሳለ ሙሽሪኮች (አጋሪዎች) በመንገድ ላይ አገኙት።

       የት እየሄድክ ነዉ ? ብለዉ ጠየቁት እሱም ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምን ፈልጎ(ለሲለም) መሆኑን ነገራቸዉ።እነሱም "ወደሱ(ወደ ረሱል) አትድረስ ምክንያት እሱ ሶላትን)ስግደትን ያዝሀል" አሉት፣ እሱም ለፈጣሪ መታዘዝ ግዴታ ነዉ ኣላቸዉ። አሁንም እነሱ "ሀብትህን ለድሆች እንድትሰጥ ያዝሀል" አሉት። እሱም መልካም ስራን መስራት ግዴታ ነዉ አላቸዉ።

      በድጋሚ "እሱኮ ከ ዚና(ዝሙት)ይከለክልሀል" አሉት፣ እሱም ዚናኮ በጭንቅላት ስናስበዉ ራሱ አስጠሊታና እጅግ ፀያፍ ነዉ፣ እኔም ደግሞ ትልቅ ሰዉ ሆኛለዉ(አርጅቻለዉ) ስለዚህ አልፈልገዉም አላቸዉ። በመጨረሻም ከኸምር(አስካሪ መጠጥ) ይከለክሉሀል ተባለ አዕሻም በዚህ ሰዓት ይሄማ(አስካሪ መጠጥ) አልታገስበትም(አልተወዉም) በማለት ተመለሰና አንድ አመት አስካሪ መጠጥ ጠጥቼ ተመልሼ መጣና እስልምና እቀበላለዉ አለ። ከዛም እየተጓዘ ወደ ቤቱ ሳይደርሰ ከግመሉ ላይ ወደቀና አንገቱ ተሰብሮ ሞተ!

ምንጭ :- አል-ኢስቲዕያብ ፊ ማዕሪፈቲል አስሀብ (1748/4)

-------------------------------

- በህይወት እያለህ ሁለት ለየት ያሉ አጋጣሚዎች ይመጡልህ ይሆናል፣ አንዱ ምርጥ ሲሆን አንዱ ክፉ አጋጣሚ ነዉ። አንዱ አጋጣሚ ከወንጀል በኋላ ሞት ነዉ ማለትም ወንጀል እየሰራህ ነገ ተዉበት አስከትላለዉ ብለህ ሳይሳካ ይቀርና ሞት ይቀድምሀል ከዛ ወንጀለኛን ሚከተለዉ ይከተልሀል።

-ሁለተኛው ከተዉበት በኋላ ሞት ሲከተል ማለትም አላህን እያመፅክ ኖረህ በመጨረሻም ተፀፅተህ ተዉበት አርገህ በንፁ ልብ ወደ አላህ እንደመመለስ እድል የለም። ከዛ ለመልካሞች የተዘጋጀውን በአላህ ፍቃድ ታገኛለህ።

وَاسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ ثُمَّ تُوبُوا إِلَيْهِ ۚ إِنَّ رَبِّي رَحِيمٌ وَدُودٌ

[ ሱረቱ ሁድ - 90 ]

«ጌታችሁንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ ከዚያም ወደርሱ ተመለሱ፡፡ ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነውና (አላቸው)፡፡

"ሞት ያንተን መስተካከል አይጠብቅም

             አንተ ተስተካክለህ ሞትን ጠብቀዉ"

✍Abu Atikah

https://t.me/Ibnusulymaan123

Telegram: Contact @Ibnusulymaan123

Telegram: Contact @Ibnusulymaan123

ይህ ቻናል ሙስሊም ባልሆኑ አካለት እሥልምና ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ንፅፅራዊ ምላሾችን የሚሰጥ እና የእስላማዊው ትምህርቶችን የሚተላለፍበት ነዉ የ ᴛɪᴋ ᴛᴏᴋ ᴀᴄᴄᴏᴜɴᴛ https://vm.tiktok.com/ZM2g4A23E/ ለሀሳብ እና ጥያቄ @Abuatikah110 @Responser16
Send as a message
Share on my page
Share in the group