6 ай Тәрҗемәсе
Татарчага аудару мөмкин түгел.

የቀሳም ብርጌዶች ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ አሁን ከመሸ የሰጠው መግለጫ

- የወራሪዋ ጦር በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችንና ህጻናትን ደም በማፍሰስ መስጊዶችን፣ ሰላማዊ መኖርያዎችን፣ ትምህርት ቤቶችንና ሆስፒታሎችን በቦምብ በማጋየት ለ5 ሳምንታት ነውሩን ለመሸፈን ሞክሯል።

- ጠላት በአለም ፊት የፈፀመው እልቂትና የዘር ማጥፋት ዘመቻ የዚህ ጦርነት ብቸኛ ስኬቱ ነው።

- እነሆ በጋዛ የእግረኛ ጦር ፍልሚያ የጽዮናዊ-አሜሪካዊ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች ቀስ በቀስ እየተደቆሱና እየወደሙ ነው።

- የወራሪዋ ታንኮች ወደ ኋላ እንዲያፈገፍጉ እና የወረራውን አቅጣጫ እንዲቀይሩ የሚያስገድዳቸው ኃይለኛ ተቃውሞና ከባድ ፍልሚያ ገጥሟቸዋል።

- ተዋጊዎቻችን ከመሬት በታችና ከፍርስራሽ ስር ወጥተው ጦርና  ጋኖቹን እያወደሙ ወታደሮችን እየገደሉ ይመለሳሉ።

- በ48 ሰአት ውስጥ ከ25 በላይ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉና በከፊሉ ማውደማችንን እንገልፃለን።

Send as a message
Share on my page
Share in the group