Translation is not possible.

➾ነሲሀ ለራሴ እና ለእህቶቼ

እህቴ ተመከሪ  ሰዎች ወደ ገደል እየገቡ ባለበት ሁኔታ መካሪ ካገኘሽ ተመከሪ

ካልሆነ ግን

ምከረው ምከረው እምቢ ካለ.....  ነው የሚሆነው ነገሩ

እናማ እህቴ ምን ልልሽ ፈልጌ ነው

እኛ ሴቶች ልባችን በትንሽ ነገር ትታለላለች ሰውን (ወንድን) የማመን ባህሪያችንም በጣም የጎላ ነው።

በተለይ በዲን ስም ከመጣ በሚዲያ ተውሂድ ሱና እያለ የሚያወራ ከሆነ በቃ ልባችን ትሸነፋለች ግን መሆን የለበትም።

አዎ ተውሂድን በማሰራጨቱ ልናደንቀው እንችላለን ግና ይህችን ልምዱን ብቻ ይዘን ሙሉዕ ነው ብለን ማሰብን መተው አለብን ይህ የብዙዎቻችን ችግር ነው።

አዎ በዚች ምድር ላይ ሰው ሆኖ ሙሉዕ የሆነ የለም ነብዩ ﷺ ሲቀሩ

እናማ እህቴ በሚዲያ ለጮኸ ሁሉ አትሸንገይ ወሏሂ ወቢላሂ ወተሏሂ የምነግርሽ ነገር ቢኖር አሏህ ካዘነላቸው ውጭ ብዙዎቹ የሚዲያ ጀግኖች ቤታቸው ውስጥ ቁርዓን እንኳን አንስተው የማይቀሩ ባዶ ናቸው።

እየዋሸሁ አይደለም በአይኔ ካየሁት እና ከሰማሁት እንጂ

እህቴ ማንን ማግባት እንዳለብሽ በደንብ ልታስቢበት ይገባሻል ብዙ እየሰማን እና እያየን ነው በሚዲያ ታዋቂ ስለሆነ ብቻ ማንንም ስለሱ ምንም ሳትጠይቅ ሀታ ቢነግሯት እንኳን ምቀኝነት እየመሰላት "ተውኝ እሱ እናንተ እንደምታስቡት እና እንደምትለሉት አይደለም" እያለች ባህሪው ምንድን ነው እንኳን ብላ ሳታጣራ እየገባች መጨረሻዋ ለቅሶ ይሆናል።  ይሄ አያዋጣም መጀመሪያ ነው ማሰብ

አዎ አሏህ የወሰነው በእርግጥ አይቀርም ግን ሰበቡን ማድረስ አለብን በዲኑ ስለተማረክሽ ብቻ "ካላገባሁህ" ብለሽ መቀመጪያ አታሳጪው እሱም ደግሞ "ጠይቃኝ እምቢ ብያት" እያለ እና እየተኮፈሰ ለሌሎች እንዲወራብሽ አትሁኚ

ሲጀመር እህቴ መጠየቅሽ አደብ አይደለም አዎ መረጃ ብለሽ "ኸዲጃ እንዲሁም ሌሎች ሰሀቢቶች ረሱልን ﷺ ጠይቀው የለ እንዴ!? " ልትይኝ ትችያለሽ

አዎ ይህንን አልክድም ግን እኮ እህቴ አስተውለሽ ከሆነ ሰሀቢቶች የጠየቁት ነብይን ከአሏህ ወህየሰ የሚወርድለትን እንጂ ዛሬ አንቺ የጠየቅሽውን የሚዲያ ጀግና አይነት ሰው አልነበረም ነብይን አይደለም ጥቂት ሴቶች ሁሉም ቢጠይቁ አይገርምም ምክንያቱም ነቢይ ስለሆነ ግን ዛሬ አንቺ ያበድሽለትን አይነት ወንድ ውጭ ባህሪውን ሳታውቂ በዲኑ ላይ ያለውን ጥንካሬ (ቤት እና ኢባዳዎች ላይ) ሳታውቂ በሚዲያ ስለጮሀ ብቻ መጠየቅሽ ገርሞ የሚገርም ነገር ነው።

ሀቂቃ እህቴ ስለማዝንልሽ ነው ይህን የምልሽ ይሄ አሳፋሪ ተግባር ነው ለወንዶችም የልብ ልብ መስጠት ነው። እናም ይህን አይነት ባህሪን አትላበሺ ሀያዕ ይኑርሽ አሏህ ላንቺ የፃፈው አለ ማንም አይወስድብሽ አንቺ ግን ሰብር አድርጊ አሏህ ካላለው ስለጠየቅሽውም ላታገቢው ትችያለሽ

እናማ ውዷ እህቴ "ትዳር ጌም አይደለም" እና በደንብ አስቢበት

ማነው?   ባህሪውስ ምንድነው?  ለኔስ ይሆነኛል? እኔ በዲኔ ስዳከም የሚያጠናክረኝ ነው ወይስ?

እነዚህን ጥያቄዎች አስምሪባቸው።

እህት ተመከሪ ያየ እና ያወቀ ይምከርሽ

ለናሙና ያክል ይህን ካልን በቂ ነው ብልጥ ሴት ጥቆማ ይበቃታል!!

https://t.me/deawa_selefiya

Telegram: Contact @deawa_selefiya

Telegram: Contact @deawa_selefiya

የታላላቅ ዳኢዎችን ፈዋኢድ የሚያገኙበት ቻናል ነው።ይቀላቀሉ።
Send as a message
Share on my page
Share in the group