በዚህች አለም ውስጥ ህይወት ትቀጥል ዘንድ የህይዎት ማራዘሚያ ነው። ሰዎች ነገን ያልሙ ዘንድ የነብስ ስንቅ ነው። የስኬት ሰዎች ለስኬት ከበቁባቸው መንገዶች ውስጥ ቁልፉን ሚና የሚጫወተው እሱ ነው። የህይወት ማጣፈጫ ቅመሞች ውስጥ ዋነኛውና ወደር የለሹ ነው። #ተስፋ
የሰው ልጅ ከሰው በታች ሆኖ ራሱን ከጣለ፣ የህይወትን ጣዕም ማጣጣም አቅቶት ህይዎት ቆቅ ካለው፣ የውድቀት ተምሳሌት እስኪሆን ድረስ ላይነሳ ከወደቀ፣ የገዛ ነብሱን እስከ ወዲያኛው አለም ድረስ ከሸኘ፤ አትጠራጠር የዚህ ሁሉ ምክንያት የተስፋ ማጣት ነው።
አንድ ሰው ከወደቀበት ሊነሳ፣ ከዛሬ አልፎ ነገን ሊያልም፣ የዛሬን እንቅፋት ሊሻገር፣ ነብሱ በወኔ ሊሞላ ዘንድ፤ ተስፋ ሊኖው ግድ ይላል!
የጀሃነም ሰዎች ከሚቀጡት ቅጣት ሁሉ ከፍተኛው፤ የጀነትም ሰዎች አላህን ከማየታቸው በመቀጠል ከፍተኛው ሽልማታቸው ምን እንደሆነ ታውቃለህ? አዎ ተስፋ ነው።
የጀሃነም ሰዎች ከሚቀጡት ቅጣት ውስጥ ትልቁ ተስፋ ማጣት ነው። ከጀሀነም ፈፅሞ አንወጣም በሚል ተስፋ መቁረጥ። የጀሃነም ሰዎች በምድር ላይ ባለው አሸዋ ልክ ተቀጥታችሁ ትወጣላችሁ ቢባሉ፤ በዚህች ተስፋ ብቻ የጀሃነምን ቅጣት ለመቋቋም በቻሉ ነበር። ያ ግን ፈፅሞ ሊሆን የማይችል ነው። ምክንያቱም ላይወጡ ገብተዋል፤ ላይሞቱ ነቅተዋልና!
የጀነት ሰዎችም ጀነታቸው ጣፋጭ እንድትሆንላቸው ከሚያደርገው ውስጥ አንዱ ተስፋ ነው። ከጀነት ፈፅሞ አንወጣም የሚል ተስፋ!
በዚህች ምድር ላይም ተስፋ ወሳኙ ቁልፍ ነው። የሰው ልጅ በየትኛውም መልኩ ተስፋ ሊቆርጥ አይገባም። ምድር በለውጥ ማዕበል የምትናጥ መርከብ ናት። በዚች ምድር ለውጥን በውድም ይሁን በግዱ የማያስተናግድ የለም። ዛሬ የከበደህ ነገ ይቀልሃል፣ ዛሬ የቸገረህ ነገ ይተርፍሃል፣ ዛሬ ያጣሃው ነገ ይኖርሃልና ተስፋ አትቁረጥ! አላህ ይህን ሊነግረን እንዲህ ይላል፦
{إِنَّ مَعَ ٱلْعُسْرِ يُسْرًۭا}
"ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡" [አል ኢንሽራህ: 6]
አዎ ከችግር ጋር ምቾት አለ። ከማጣት በኋላም ማግኘት፣ ከሃዘን በኋላ ደስታ፣ ከመናቅ በኋላ መከበር አለና ተስፋ አትቁረጥ።
ተስፋ መቁረጥ የሰነፎች መተዳደሪያ ደንብ፣ የክስረት ሰዎች መለያ ምልክት ነው።
Copied with some correction.