Translation is not possible.

《 እኛና የዱኒያ ህይዎት》

በክራይ ቤት እየኖርን ባለቤቱ መጥቶ

-ቀደሞ ካሳወቀን በሗላ- ቤቴን ለቀህ ውጣ ጊዜህን ጨርሰሃል ቢለን አልወጣም እንደማንለው ሁሉ

ሀያሉ ጌታችን አሏህ

(كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ ِ)

[ ነፍስ የተባለች በሙሉ ሞትን ትቀምሳለች ዋጋቹን የምታገኙት የቂያማ ቀን ነው ] ብሎ ከነገረን በሗላ

አጀላችን ሲደርስ መለከል መውት መጥቶ ነፍሲያችንን ከሰውነታችን መዞ ስያወጣት አልወጣም ማለት አትችልም!

ይህን ሁሌም እናስታውስ ልብ እንበል ሞት ለማንም እንደማይቀር ሁላችንም እናውቃለን ነገር ግን በድንገት ሊመጣ እንደሚችል አብዛኞቻችን እንዘነጋለን። በዚህም ምክንያት ከጌታችን ጋር ያለን ግንኙነት የተበላሸ ይሆናል ።

የማይቀርበት ጉዞ ነውና ለራሳችን እና ለምንወዳቸው ቤተሰቦቻችን አላህ መጨረሻችን/ቸው እንዲያሳምርልን/ላቸው በዱዓ እንለምነው።

Send as a message
Share on my page
Share in the group