Translation is not possible.

ከሰላም ከጤና የበለጠ ምን አለና نسآلوالله العفية🤲

ጣፋጭ የተባለን ነገር ሁሉ ቀምሻለሁኝ ነገር ግን 👉ጤናን ሰላምን👉የመሰለ ጣፋጭ ነገርን ግን አልቀመስኩኝም።

ከሷሊህ ከደጋጎች ንግግር የተቀነጨበ🍀

አዎን አላህ ያዘነልን ስንቀር እኛ ሰዎች ስንባል ከጤንነትም ከሰላምም በላይ ደስተኛ ያደርገናል ብለን የምንመኛቸው ዱንያና ስልጣን ናቸው ነገር ግን ዱንያ የተሰጠው ሁሉ ደስተኛና ሰላማዊ ህይወትን ተጎናፅፏል ማለትን አይቻልም፣

አዎን ገንዘብ ከኢማን ከአፍያ ጋር የተለገስክ እንደሆን በእርግጥም ደስተኝነትና ጣፋጭ ህይወትን ልትለገስ ትችላለክ በተሰጠክ አመስግነክ ባለህን ተብቃቅተክ የኖርክ እንደሆንክ👇

በተቃራኒው ጤንነትና ሰላምን ተለግሶ ይህንን ውድ ንብረት አርክሶ በመመልከት በተሰጠውን ተደስቶ ባለውን ተብቃቅቶ ባጣውን ሰብር አድርጎ ያልኖረ እንደሆነ በእርግጥም በእጅ ያለን ወርቅ እንደ መዳብ መቁጠሩን ዋጋ ያስከፍላልና ለዚህም ክህደትና ማማረርክ ዋጋ እያስከፈለክ ትኖራለክ❗❗

እወቅ ብዙ ግዜ በጤና መታወክና ከአሁን አሁን እንዳለኝ የተገነዘበ ጠላት አጠቃኝ እያለ ያለ እንቅልፍ ሚያነጋው ሀብታሙ ነው፣

እወቅ ብዙ ግዜ የምቾት ሀያት ከሚያጡት መካከል ባለ ስልጣኑ መሆኑን ከአሁን አሁን መፈንቅለ ሊደረግብኝ ከስራዬ ተቀናቃኝ ይመጣብኝ እያለ በተሰጠው ስልጣን ምቾቱን እየነሳው ይኖራል፣

ስለዚህም አመስግን አታማርር ጌታችን الله እንዲህ በማለት አዞናልና👇

لإن شكرتم لآزيدنكم ያመሰገናችሁኝ እንደሆን እጨምርላችጟለሁኝ።

አዎ ከአመስጋኞችም ያድርገን ጀሊሉ ሰላትና ሰምም በውዱ ነብይ በረሱሉና ሙሀመድ صلى الله عليه وسلم ላይ ይውረድ🌹

አቡ ማሂ Mk ነኝ የተማሙ👇

https://t.me/httsibnutemamAbumahi114

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group