Translation is not possible.

ሰውየው በአላህ ቅጣት እና በክስረት ውስጥ እየኖረ የደረሰበትን አደጋ ላያውቅ ይችላል።

ቅጣቱ ነፍሱን መርሳቱ ነው። ለነፍሱ የሚበጃትን አያውቅም። ነውሯን አያውቅም። እንዴት ከቆሻሻዋ ልትፀዳ እንደምትችል አይረዳም። በሚጎዱት ነገሮች ይጠመዳል። ለህይወቱ ከሚጠቅሙት ነገሮች ይርቃል።

:

አስተውል!

[وَلَا تَكُونُوا كَالَّذِينَ نَسُوا اللَّهَ فَأَنسَاهُمْ أَنفُسَهُمْ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الْفَاسِقُونَ]

«እንደነዚያም አላህን እንደረሱትና ነፍሶቻቸውን እንዳስረሳቸው (ሰዎች) አትኹኑ፡፡ እነዚያ እነርሱ አመጸኞቹ ናቸው፡፡»

የጀመሩት እነርሱ ናቸው። አላህን ረሱ።

በውጤቱ አላህም ነፍሳቸውን እንዲረሱ አደረገ። የመድኅን መንገዳቸውን፣ የደስታውን ጎዳና ሸፈነባቸው።

(Tofik Bahiru)

Send as a message
Share on my page
Share in the group