ተመልከት!!
ከተወለድኩበት-ካደግኩበት ቀዬ
አፍ ከፈታሁበት-ከለመድኩት ዘዬ
በእምነቴ ተገን-በግፍ ተነጥዬ
ተራቁተሽ ካልሄድሽ-አትጠቅሚም ተብዬ
የእምነቴን አርማ-እንድጥል ታልሞ
ያደረሱት በደል-በልቤ ታትሞ
አለሁ እስከዛሬ-ተስፋ እንደሰነቅኩ
ልቤን በአላህ ነስር ላይ-እንዳንጠለጠልኩ
ግን ምንምም ቢሆን-በደሉ ቢከፋ
መቼም ግን አንቆርጥም-በአላህ ላይ ተስፋ!!
//////////////////////////////////////
👉፦አድምጠኝ ልንገርህ -የሙስሊም ሴት ጠላት
ይሄ አዱንያ ነው-አትዘወትርበት
ይሄ ከንቱ ስልጣን-ጀነት አትገባበት
"ወንበር"ም በጊዜው-ቀኑ ከደረሰ
ይሰበራል ቶሎ-እንደበሰበሰ‼️
ክፉ ተናግሬ-የበደልህ ልኬት
እኔ አላሳይህም-እንዲሰማህ ሀሴት
ቁስሌን ከፍቼ-ተመልከት አልልህ
እንድትሳለቅም-እድልም አልሰጥህ።
//////////////////////////////////////
ድሮ እኔ የማውቀው...........
ከሞተ ኋላ ነው-ሰው ምስጥን ሚበላ
ታድያ እንዴት መነነ-በቁም ያንተ ገላ
በግርህ ስትራመድ-በልተህ እየጠጣህ
ፀፀት ነው መሰለኝ.......
የክፋትህ ውጤት-ከሰውነት ተራ ነጥሎ ያወጣህ!!
በስልጣንህ ሽፋን-ቃልህ ስታጎድል
ያመነህን ክደህ-ትክክል ነኝ ስትል
በውሸት ለዚያውም-በአደባባይ ስትምል
ያኔ ነው ያወቅኩት-የስልጣንን ክፋት
ጥቅምና ጉዳቱ-መወደድ መጠላት
ያኔ ነው የገባኝ-የጥላቻህ መጠን
ውጤቱ ይኸው ነው-ድሮም ሰውን ማመን!!
////////////////////////////////////
👉:-አሁንም ል-ን-ገ-ር-ህ.......
አቃለሁኝ እኔ ብዙ መናገሬ-ስሜት አይሰጥህም
ስለ ሙስሊም ሴት ልጅ-ቅንጣት አይገድህም
ተራቁቼ ብሄድ-ደስታህ ወደር ያጣል
ለነገሩ ድሮስ....
ለሆዱ ከሚያድር-ምን ኸይር ይጠበቃል!?
ግን አንተ በፃፍከው-እንደ ህግ አርቅቀህ
በሴኩላሪዝም ሂጃብ-የለም ብለህ
ሸፋን እያደረግክ-ከለከልከኝ ብዬ
ራቆት አልሄድም-እኔ "ኒቃብ" ጥዬ!!
እመነኝ ግድ የለም........
መማሬ አይቀርም-በአራዳም በፋራ
በንዳንተ አይነቱ-ቀሽም ሳልመራ
ካለምኩት ደርሼ-ካሰብኩበት ስፍራ
ሂጃቤን ለብሼ-በኩራት ስሰራ
እመኛለሁ እኔ-እንድታይ በአይንህ
ክፉ አልናገርም-ብቻ እድሜ ይስጥህ!!
Comment has been successfully reported
The post has been successfully added to your timeline!
You have reached your limit of 100000 friends!
File size error: The file exceeds the allowed limit (9 GB) and can not be uploaded.
Your video is being processed,
We’ll let you know when it's ready to view.
It's impossible to upload the file: This file type is not supported.
We have detected adult content on the uploaded image,
therefore we have declined the uploading process.
To get a verification (tick) on the Islamic social network Umma Life, you must meet at least one of the following criteria: 1. Social network activity: Participants seeking verification must be active users of the social network. At least one useful message must be posted per day, and the message topics can be non-religious. 2. A well-known Islamic blogger or Muslim: If you are a well-known Islamic blogger or Muslim, even if your activities are not related to religious topics on the Internet, you can also apply for verification. 3. A large number of subscribers or active religious pages: If you have a lot of subscribers on social networks or you actively manage useful religious pages, this can also be a basis for getting verified. If you meet at least one of these criteria, submit an application for verification on the Islamic social network Umma Life via private message https://ummalife.com/ummalife and your account will be reviewed by the social network administration.