➣ ኋላህን መለስ እያልክ እያስታወስክ!
ክፍል 1
ትላንት አሁን ባለህበት ሁኔታ ሳትሆን በፊት ስትመኛቸው የነበሩ ነገሮች ዛሬ ተሳክቶልህ በእጆችህ የመስራት እድሉን ስታገኝ ሊያሰናክሉህ የማይገቡ ነገሮች አያሰናከሉህ! ትክክለኛ ውሳኔህንና ህልምህን አያስቀይሩህ! ትላንት ለህሊናህ ታማኝ ሆነህ ብዙ መስራት ሀሳብ የነበረህ ሰው ዛሬም ቆም ብለህ አስብና ህልምህን ሙላ! መጥፎ ህልም ከነበረህ ቀይረውና ለትልቅ ነገር አውለው! ስኬት ላይ ደርሰህ ብዙ መልካም ነገሮች መስራት እየቻልክ አንዳንድ ሁኔታዎች ተከትለህና በጥቃቅን ነገሮች ትኩረትህ ተሰርቆ እንዳያዛንፉህ! ከማነም ጋር ራስህን ሳታወዳድር መልካም ነገር ሁሉ የሚገኝብህ ትልቅ ሰው ለመሆን ጥረት አድርግ!
እወቅ! ትክክለኛ የሆነ መልካም ነገር በየትኛውም መለኪያ መልካም ነው። ይህችን ሀሳብ በውስጥህ ከቋጠርክ ሁል ጊዜ መልካም ታገኛለህ! ሌላም የማታውቀው መልካም ነገር ይገጥምሃል።
አንተ በሸሪዓዊይ እንቅስቃሴ ላይ ያለህ ሆይ፦ህልምህ ምን ነበር? ገና ከዚህ ሳትደርስ፣ ገና የሸሪዓን ሽታ ለማሽተት ስትነሳ፣ ከዛም ጠለቅ እያልክ ስትገባ መልካም ንያዎችህም እየሰፉና እየተዋቡ ሲመጡ!? ታዲያ የዛኔው ህልምህና የዛሬው ስኬትህ የትና የት ነው? ተለያየ ወይስ አንድ አይነት ሆነ? በየት ዙረህ መጣህ? ወይ በመጥፎ የአስተሳሰብ በሽታ መቼ ተመረዝክ? ወይስ ከጠበከውም በላይ ትልቅ ነገር ገጠመህ!? ከአሁን በኋላስ ወደ የት እየሄድክ ነው? አደራህን ሁል ጊዜም መለኪያህን አሳምር! በጥሩ መለኪያ ከለካህ መጥፎና ደጉን ትለያለህ! አደራህን የነበርክበትን ትክክለኛ የሆነ መልካም ነገርን ተሸውጀ ነበር ብለህ ከመተው! በተቻለህ የሰዎችን ሙገሳና ውደሳ እንዲሁም ጭብጫቦ ከመከተል ተጠንቀቅ! ይሄ የመልካም ህልሞችን መስመር የሚያቋርጥ ከብዙዎች ዘንድ ያልተባነነበት በሽታ ነው። በተቻለህ የራስህም ነፍስያ ስታወድስህ ለመከላከል ጥረት አድርግ! ሰዎችን ደርሰህ አትናቅ! ማንኛው ትልቅ ደረጃ እንዳለው አታውቅም። አዎ ምናልባትም የትላንት መልካም ህልምህን እውን የሚያደርግልህ የምትንቀውና ጉዳይ የማትሰጠው ሰው ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ሰዎችንም ከልክ በላይ አጋነህ አትሰቃቅል! የመካሪን ምክር በምክሩ ይዘትና ልክ እንጅ፣ በሰዎች ማንነት ተሸውደህ የተለያየ ግምት አትስጠው! ከአጉል ጥርጣሬ ተቆጠብ ጥርጣሬ የተሳሳተ ውሳኔ ያስወስንሃልና! ሁሉም ይሳሳታል በረካታ የሆኑ ግዙፍ ስህተቶች ሊከሰቱብህ ይችላሉ። ታዲያ ትልቅነትህ ስህተትን አምነህ ማስተካከልህ ነው። በዚህ ጊዜ አላህ ከፍ ከሚያደርጋቸውና እያደር ከሚደምቁ ሰዎች ያደርግሃል። ስህተትን ለማረምና በሌሎች ሰዎች ለመታረም ሁል ጊዜም ክፍት ሁን! የትክክለኛ ህልም ዋና የስኬት ቁልፍ ይሄ ነውና።
ለዛሬው ከዚህ ይብቃና የአላህ ፈቃድ ከሆነ ክፍል ሁለት ይቀጥላል!
✍ አብዱረህማን ዑመር
የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ
https://t.me/Abdurhman_oumer/4806