Translation is not possible.

"ሡልጣን ሆይ! ሰላትህን በጀመዓ አትሰግድምና ምስክርነትህ ተቀባይነት የለውም..."

╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍╍

  አሁን የምንገኝው በሙስሊሞች ዋና ከተማ ቡርሳ ነው። በታላቁ መሪ በሱልጣን ባየዚድ ቢን ሙራድ ዘመነ መንግስት!

ቡልጋሪያን፣ ቡርሳንና አልባኒያን ድል አድርጎ የከፈተው የክፍለ ዘመኑ ኃያል መሪ ቃዲ ሸምሰ ድ-ዲን ዘንድ በአንድ ጉዳይ ላይ የምስክርነት ቃሉን ሊሰጥ ከፊታቸው ተጥዷል። እንደማንኛውም ምስክር እጆቹን አጣምሮ ከችሎቱ ፊት ቆሟል።

ዳኛው ዓይኑን አማትሮ ሡልጣኑን እየተመለከተ ከእግር እስከ ራሱ በትኩረት ቃኘ

  "ሡልጣን ሆይ!" አለ ዓይን ዓይኑን እያየ። ታዳሚው በዝምታ ተውጦ የዳኛውን ንግግር ለመስማት ጆሮውን ቀሰረ "ሡልጣን ሆይ! ሰላትህን በጀመዓ አትሰግድምና ምስክርነትህ ተቀባይነት የለውም። ሰላቱን በጀመዓ የማይሰግድ በምስክርነት ቃሉ ሊዋሽ ይችላልና አይታመንም ተብሎ ስለሚገመት ያንተን ምስክር አንቀበልህም ሂድ" አሉት።

  በፍርድ ቤቱ የተገኙ የዳኛውን ንግግር የሰሙ ታዳሚያን በድንጋጤ አይናቸውን ለጠጡ። ሡልጣን ባይዚድን በሰዎች ፊት ዝቅ ያደረገውን ዳኛ መጨረሻ ለማየት፣ ለዳኛው እየፈሩ ባሉበት ቦታ ተቀመጡ።

ችሎቱ ፀጥ ረጭ አለ። ሡልጣን ባየዚድ አንዲትም ቃል ከአፉ ሳያወጣ አንገቱን ከመሬቱ እንደደፋ በእርጋታ እየተራመደ ፍርድ ቤቱን ለቆ ወጣ። በዚያው ቀን ከቤተ መንግስቱ አጠገብ መስጂድ እንዲሰራ አዘዘ። ተገንብቶ እንዳለቀ ሰላቱን ሳያዛንፍ አምስቱንም አውቃት በጀመዓ የሚሰግድ የአላህ ባርያ ሆነ።

ይህ ፍትህ የንግስና መሰረት፣ የኢስላም ዳኞችና ዑለማኦች ከአላህ በቀር ማንንም በማይፈሩበት ወቅት የተገኘ አስገራሚ ታሪክ ነው::

Send as a message
Share on my page
Share in the group