Translation is not possible.

👆👆ጨለፊይ «ረሱል ከየሁዳዎች ጋር ተዋውለዋል» ካለህ አልተዋዋሉም በለው። ምክንያቱም እርሱ በዚህ የማስረጃ አቀራረቡ የሚፈልግበት መሪዬ የሚላቸው ሰዎች ከኢስራኤል ጋር የሚያደርጉትን ስምምነት ረሱል ያደረጉት አይነት ስምምነት ለማስመሰል ነው።

ኢስራ&ኤል ደውላ ሙሓሪባ ናት። በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ ጦርነት ያወጀች ትልቅ ትንሽ ሳትል አሰቃቂ ጭፍ&ጨፋ የምታካሂድ ጠ%ላት ሀገር ነች። ረሱለላህ ﷺ ሙስሊሞችን ከተዋጋ የሁዳ ጋር ስምምነት አድርገው አያውቁም!

እንዴት!? እሳቸው አላህ ሲገልፃቸው «እናንተን የሚያስቸግራችሁ ነገር የሚከብድበት» ብሎ የገለፃቸው ነብይ ሙስሊሞችን ከሚገድል ጋር ስምምነት ያደርጋሉ ተብሎ ይታሰባል ?  በፍፁም! 

ይልቁንም፦  የአላህ መልእክተኛ ﷺ የበኒ ቀይኑቃእ የሁዳዎች በአንዲት ሴት ሒጃብ ላይ ቢረማመዱ ጂሃድ አውጅው ከመዲና ነው ያባረሯቸው! 

የበኒ ቁረይዟ የሁዳዎች ከመካ ሙሽሪኮች ጋር ተባብረው ሙስሊሞችን ለመጨፍጨፍ በመስማማታቸው ውላቸው ስለፈረሰ በአንድ ቀን አራት መቶ የሁዳ አንገታቸውን ነው የበጠሱላቸው!

የበኑ ነዲር የሁዳዎች ሶስት ሰሃቦችን ቃላቸውን በማፍረስ ቢገድሏቸው ረሱለላህ ﷺ «አስር ቀን ብቻ ሰጥቻችኋለሁ መዲናን ለቃችሁ ውጡ! » የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥተውና ጂሃድ አውጀው አንድም መሳሪያ ሳይዙ ቤታቸውን እያፈረሱ ከመዲና እንዲወጡ ነው ያደረጓቸው!

ይህን ዘመቻ በማስመልከት ኢብኑ ዐባስ (ረዐ) «ሱረቱ በኒ ነዲር » ብሎ የሚጠራት ሱረቱል ሐሽር ምእራፍ ወረደች። በውስጧም የጠላትን ዛፎች መቁረጥና ማቃጠል አላህ የፈቀደበት ብይን ወረደ።

ምን እንደ ህዝብ በግለሰብ ደረጃ ከዕብ ኢብኑል አሽረፍ የሚባል የሁዲ በስነ ፅሁፍ ክህሎቱ የሰሃባ ሚስቶችን ቢፎግር አራት ጀግኖችን ልከው ጭንቅላት የከበደውን አንገት ሸክሙን ቀለል አደረጉለት! 

ከዚህ ሁሉ በኋላ ይመጣና የሁዳዎችን በቁርኣንና በሰይፍ የተዋጋን ነብይ ከየሁዳዎች ጋር አድርጎት የነበረን ስምምነት ለየሁዳዎች የአየር ሃይል መነሻ ጦር ቤዝና ነዳጅ የሚያቀርብ ኸቢስ መሪው የሚያደርገው ስምምነት ጋር ሊያመሳስል ይዳዳዋል!!

«ፈህመ ገዳዳ»  አለ አቡ ቁተይባህ! 

የሁዳ ጋር ረሱልﷺ የተስማሙት ሙስሊሞች ጋር ሙሳሊም ሆነው ከኖሩ ብቻ ነበር። ሲተናኮሉ ፈርሷል!  ስምምነቱ የተደረገውም ለሙስሊሞች ህልውና ስለነበር! 

የርሱ ከቢስ መሪ ህንፃን በህፃን ላይ የምትደነባን ተዋጊ ሀገር  በገንዘብና በሎጅስቲክ እያገዘ ሆኖ ሳለ  ስተወቅስበት ረሱል ከየሁዳዎች ጋር ስምምነት አድርገው የለ? ይልሀል።

ሸህ አብዱለጢፍ (ሐፊዘሁላህ)  እንዲህ አይነት ቀሽም ግንዛቤ ያለው ሰው ሲያጋጥማቸው አንድ የሚሏት ነገር አለች ፦

«ይህን ንግግርህን አህያ ራሱ ብትሰማ ትስቅብሀለች ዝምበል! »

Send as a message
Share on my page
Share in the group