Translation is not possible.

አይሁዶች ፍልስጤምን በሂደት ለመቆጣጠር እንቅስቃሴ ሲጀምሩ የነበረውን ሁኔታ አንድ ፍልስጤማዊ አዛውንት እንዲህ ሲል አውግቷል ፦ " አንድ አይሁድ መጣን መሬቴን እንድሸጥለት ጠየቀኝ። እምቢ አልኩት!!! መሬቴን ለመውሰድ ሲል የፈለግኩትን ያህል ገንዘብ እንደሚከፍለኝ ነገረኝ። እኔ ግን አልተቀበልኩትም!! "ባዶ ቼክ ልስጥህና የፈለግከውን ያህል ገንዘብ ቁጥር ፃፍበት" አለኝ። ሆኖም አሻፈረኝ አልኩት። 

 

"ይህቺን መሬትህን እንድትተውልኝ ምን ማድረግ አለብኝ? " ሲል ጠየቀኝ። 

 

እንዲህ አልኩት ፦ " ባዶ ወረቀት ልስጥህና ዓለም ላይ ያሉ ሙስሊሞች በሙሉ ፍልስጤም ላይ ያላቸውን ድርሻ እንዲተዉልህ እያንዳንዳቸውን አስፈርመህ ና !! ከዚያ በኋላ እኔም እተውልሃለሁ። ፍልስጤም የኔ  አይደለችም ፤ የሁሉም ሙስሊሞች እንጂ !! የሙስሊሞችን ሁሉ ፊርማ ካመጣህልኝ በነፃ እለቅልሃለሁ" አልኩት!! 

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group