Translation is not possible.

የወልቂጤ እናት ደስ ይበልሽ ዛሬ!!

የወልቂጤ እናት ደስ ይበልሽ ዛሬ

ልጆችሽ ተባብረው አፍርተዋል ፍሬ።

እንዲህ ነው ልጅ መውለድ መልሶ ይክሳል

ከችግር በኋላ ታሪክ ይቀይራል።

ከብዙ ጥበቃ ከናፍቆት በኋላ

በወልቂጤ ምድር ብስራት ተሰማ።

ተውሒድ እንዲያብብ እንዲበራ ሱና

መስጂዱ ተከፍቷል

ሓያ ዓለል ተውሒድ በልና ተጣራ።

ስቴድ ወደ ጅማ ወይም ወደ ቋንጤ

ማረፍህ አይቀርም ውቢቷ ወልቂጤ።

ወልቂጤ ሲታወስ በሁሉም ልብ ላይ

ከክትፎ ሚጣፍጥ ዳዕዋ ተጀምሯል።

በዚህ መስጂድ ጉዳይ የቆማችሁ ሁሉ

እንኳን ደስ ያለችሁ

ፍሬው በስሏልና ቀንጥሳችሁ ብሉ።

አላህ ከችሮታው እጥፍ ድርብ አርጎ

ጀነት ይመንዳችሁ ምንዳው አሳድጎ።

እዚህ ስትገነባ ይህን በብሎኬት

ተገንብቶ አልቋል ያንተው የጀነት ቤት።

የወልቂጤው ወጣት ጆሮህ ስጠኝ አንዴ

ታናሽ ለታላቁ ይመክራል አንዳንዴ።

ተዘርግቶልሃል ከጠላትህ መረብ

ተብትቦ ሊያስርህ በዘር አስተሳሰብ።

እንዳትጭበረበር ለፖለቲከኛ

ሙስሊም አይጃጃልም አይሆንም ዘረኛ።

ጥንብ ናት ተብለሃል ውጣ ምን አግማማህ

ኢስላም ነው ለአንተ ክብር ንፅህናህ።

በቁርኣን ተሳሰር ሁሉንም ተውና

መርህህ እንዳይሆን ጉራጌ ቀቤና።

ከጉራጌ ይሁን ወይም ከቀቤና

በተውሒድ ተዛመድ ተዋደድ በሱና።

አያምርም በሙስሊም ለዘሩ መጋደል

የተውሒድ ወንድሙ ለዘር ብሎ ማግለል።

አደራ አደራ አደራ ለእናንተ

በብሄር መቧደን አያምርም በእናንተ!!

🖌ሐምዱ ቋንጤ

ከፉርቃን ሰማይ ስር!!

የወልቂጤ መስጂድ ማስከፈቻ 25/02/16

https://t.me/hamdquante

👇👇👇

https://t.me/httsibnutemamAbumahi114

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group