7 month Translate
Translation is not possible.

"የቦምብ ድብደባውን አቁመው ለጋዛ ሕዝብ ሰላም ቢሰጡትና ችግሮችን በሰላም ቢፈቱ ለሁላችንም የተሻለ ነው።" Hassen Nasrallah

ሆስፒታሎችን፣ ት/ቤቶችን፣ የመኖሪያ ህንፃዎችን፣ መስጂዶችን፣ ቤተ ክርስቲያናትን፣ ሌላው ቀርቶ ከቀያቸው አፍናቅለው በገዛ ሀገራቸው ስደተኛ አድርገዋቸው ሲያበቁ የተጠለሉበትን የስደተኛ ካምፕ... እነዚህ ሰይጣን የሚቀናባቸው ክፉዎች ሁሉንም ነገር በቦንም በማደባየት ወደ ፍርስራሽነት ይቀይሩታል።

በዚህም በሺህ የሚቆጠሩ ንፁሀንን፣ በሺህ የሚቆጠሩ ምንም ያማያውቁ #ህፃናትን፣ ሴቶችን፣ እናቶችን፣ አረጋውያንን... ለሞትና ለአካል ጉዳት ዳርገዋል።

ክፋትና ስግብግብነታቸውን ዓለም ሁሉ እየተረዳው በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ በአፍሪካ ወዘተ በተለያዩ ሀገራት እስራኤልን በመቃወም እና ፍልስጤሞችን በመደገፍ ትዕይንተ ሕዝቦች እየተካሄዱ ነው።

የሚገርመው በአውሮፓና አሜሪካ ሕዝቡ ግፈኛዋን እስራኤል ሲቃወም መሪዎቹ ከግፍ ጋር አብረው እስራኤልን ይደግፋሉ፤ በመሣሪያና በፋይናንስም ይረዳሉ።

በተመሳሳይ እንደ አውሮፓና አሜሪካ መሪዎች እኛም ሀገር ያሉ #አንዳንድ_ክርስቲያኖች ግፈኛዋን እስራኤል ይደግፋሉ። ያለመታከት "ድል ለእስራኤል" ይላሉ። ግን አቅም ስለሌላቸው በመሣሪያና በፋይናንስ መርዳት አልቻሉም።

ይህን ሁሉ ግፍ የሚፈፅሙትን ፅዮናዊያን ለመደገፍም "መፅሐፍ ቅዱስ" በመጥቀስ ጭምር ይከራከራሉ። "የቃል ኪዳን ሀገር፣ ትንቢቱ ሊፈፀም ግድ ነው፣ ወዘተ..." እያሉ ለእልቂቱ አምላካዊ ትክክለኝነት ሊያላብሱት ይጋጋጣሉ።

ተበርቼ ሰላም አለ ስልጤ። እኔስ እንደ እነሱ በጭፍን ጥላቻ ከማብድ ዛሬውኑ ፍግም ብል እመርጣለሁ።

Injustice somewhere is injustice everywhere.

ፍትህና ድል ለተበዳዮቹ ፍልስጤሞች፣ ውርደትና ሽንፈት ለበዳዮቹ ተስፋፊ ፅዮናውያን!

"የራሷ አሮባት ምናምን" እያላችሁ እንደ እናንተ እንድንሆን ለምትፈልጉ ዘገምተኞች ደግሞ:- እኔ ሙስሊም ነኝ። ግፍና በደልን የትም በማንም ቢፈፀም እንዳወግዝ ብችል በአካልም እንድታገል ያዘዘኝ አምላኬ ነው። በዳይ እናትና አባቴ ቢሆኑ እንኳ ከተበዳይ ጎን እንድቆም ታዝዢያለሁና ሁሌም ለበዳይ ውርደትን ለተበዳይ ፍትህና ድልን መመኘቴን አላቆምም።

From the #river to the #sea #palestine will be #free 🇵🇸 💪 🇵🇸

We are all Palestinians 💪 🇵🇸

ሰላም ለሀገራችን 🇪🇹፣ ሰላም ለዓለማችን፣ ሰላም ለሰው ዘሮች ሁሉ 🇵🇸

image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group