Translation is not possible.

የፈለስጢን ውሎና አዳር‼

==================

✍ በፈለስጢኗ ጘ-ዝ'ዛ (ጋዛ) ከተማ ላይ ለተከታታይ 27 ቀናት ያላባረው የዘር ማፅዳት ወንጀልና የንጹሐን ጭፍጨፋ እንደቀጠለ ነው።

እስካሁን በወጡት መረጃዎች መሠረት፦

√ 25,000 ቶን ተቀጣጣይ ቦምብ 351 ኪሎ ሜትር² ስፋት ባላት ጠባቧ የጋዛ ከተማ ላይ የተጣለ ሲሆን ይህም 2 ኒዩክሌር ቦምብ ይሆናል ተብሏል። አስቡት! ያኔ በ2ኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የጃፓን ሒሮሽማና ናጋሳኪ በ2 አቶሚክ ቦምቦች ነበር በአሸባሪዋ አሜሪካ የወደሙት።

√ 9,061 ንጹሐን በጽዮናዊቱ እስራኤል ጭፍጨፋ ተገድለዋል፣

√ ከተገደሉት መካካል 3,760 ህፃናትና 2,326 ሴቶች ይገኙበታል።

√ 23,000 የሚሆኑ ቆስለዋል፣

√ ጠፍተዋል ተብሎ እስካሁን ሪፖርት በተደረገው መሠረት 2,060 የሚሆኑ በፍርስራሽ ስር ናቸው፤ ከመካከላቸው 1,150 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው።

√ 135 የጤና ባለሙያዎች ተገድለዋል፣

√ 25 አምቡላንሶች ወድመዋል፣

√ 100 የጤና ተቋማት በቦምብ ተመተዋል፣

√ 16 ሆስፒታሎችና 32 የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ማዕከላት ከአገልግሎት ውጭ ሆነዋል፣

√ ከትናንት በፊት በጋዛ ከተማ በሚገኘው ጀበሊያ በተሰኘው የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ 2 የሐማስ መሪዎች አሉ በሚል ጥርጣሬ ወራሪዋ ባዘነበችው ቦምብ ወዲያውኑ ከ400 በላይ የሚሆኑ በቦታው የተጠለሉ ንጹሐን ህይዎታች  ሲያልፍና በሺዎች የሚቆጠሩ ለከባድ ጉዳት ሲዳረጉ፤ እስካሁን በድምሩ ከዚያ ካምፕ ብቻ ከ1,000 በላይ ህይዎታቸው ማለፉ ተነግሯል። ይህም የጀበሊያ ጭፍጨፋ (Jabalia Massacre) ተሰኝቷል።

√ በጋዛ ብቸኛው የካንሰር ህመሙን መታከሚያ የነበረው የቱርክ ፈለስጢን ወዳጅነት ሆስፒታል በወራሪዋ ጥቃት ተሰንዝሮበት አገልግሎት በማቋረጡ የተነሳ ታካሚዎች ህይዎታቸው እያለፈ መሆኑ ተነግሯል።

√ በግብፅ አቅጣጫ የራፋ መተላለፊያ መንገድ የውጭ ሃገር ዜግነት ያላቸው ሰዎች ከጋዛ እንዲወጡ ተደርጓል፣ የተወሰኑ የጋዛ ታካሚዎች ወደ ግብፅ ወጥተው ሕክምና እንዲያገኙ ተደርጓል፣ ባይበቃም ወደ 241 የሚገመቱ የእርዳታ ጭነት መኪኖች ወደ ጋዛ ገብተዋል።

*

ይህ ሁሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ አሜሪካና አጋሮቿ አሁንም ጦርነቱ መቆም የለበትም፣ ሐማስ ከምድረ ገፅ መወገድ አለበት፣ እስራኤል ራሷን የመከላከል መብት አላት… በማለት ላይ ናቸው።

ራስን መከላከል ማለት ንጹሐንን በዚህ ደረጃ መጨፍጨፍ ማለት ነውን? አሜሪካና ወራሪዋ ይረኩ ዘንድ ስንት ፈለስጢናዊ ህፃናትና ሴቶች ህይዎታቸው ይቀጠፍ?

አላሁ-ል-ሙስተዓን!

አሁንም በዱዓችን አንርሳቸው፤ አላህ ነስሩን ያቅርብላቸው፤ አሸናፊ ሰራዊቱን ይላክላቸው።

ፎቶ፦ የጀበሊያ ጭፍጨፋ – የስደተኞች ካምፑ በወራሪዋ ቦምብ ከወደመ በኋላ

||

Send as a message
Share on my page
Share in the group