✍️أركان الإيمان !!
⏠⏠⏠⏠⏠
የእምነት መሠረቶች!!
⏡⏡⏡⏡⏡
⏞⏞⏞
↳ክፍል ⓽↲
⏟⏟⏟
«በአላህ ስሞች መገለጫ ባህሪዎች ማመን»
⭞ የአላህን ስሞችና መገለጫ ባህሪዎች ማወቅ ከእዉቀቶች ሁሉ በላጭ እዉቀት ነዉ።
⭞ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ማመን ግደታ ነዉ።
⭟ ከእምነት መሠረቶች ዉስጥ አንዱ ነዉ።
⭟ አላህን ለማወቅና ለማላቅ ትልቅ መንገድ ነዉ።
⭞ እምነት ለመጨመርና በጀነት ላይ ደረጃ ለማግኘት ምክንያት ነዉ።
⭞ ከደጋግ ሰዎች ጋር ለመቀላቀል መሰላል ነዉ።
⭟ አህሉ ሱንና በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ያምናሉ።
⭞ በጌታቸዉ ማንንም ፍጡር እንደማይመሳሰል ያፀድቃሉ።
قال تعالى:{ لَیۡسَ كَمِثۡلِهِۦ شَیۡءࣱۖ وَهُوَ ٱلسَّمِیعُ ٱلۡبَصِیرُ }
«የሚመስለዉ ምንም ነገር የለም።» እርሱም ሰሚዉ ተመልካቹ ነዉ።ይላሉ። (አሽ_ሹራ :11)
☞አላህ መልካም ስሞች እንዳሉት ተናግሯል
☛በስሞቹምይጠሩታል፣ይለምኑታል፣ይማፀኑታል።
قال تعالى:{ وَلِلَّهِ ٱلۡأَسۡمَاۤءُ ٱلۡحُسۡنَىٰ فَٱدۡعُوهُ بِهَاۖ وَذَرُوا۟ ٱلَّذِینَ یُلۡحِدُونَ فِیۤ أَسۡمَـٰۤىِٕهِۦۚ سَیُجۡزَوۡنَ مَا كَانُوا۟ یَعۡمَلُونَ }
«አላህ እንድህ ይላል፦»ለአላህ መልካም ስሞች አሉት(ስትፀልዩ) በርሷም ጥሩት። እነዚያንም ስሞቹን የሚያጣምሙትን ተዋቸዉ።ይሰሩት የነበሩትን ነገር በእርግጥ ይመነዳሉ። (አል አዕራፍ:180)
قال تعالى:{وَلَهُ ٱلۡمَثَلُ ٱلۡأَعۡلَىٰ فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰتِ وَٱلۡأَرۡضِۚ وَهُوَ ٱلۡعَزِیزُ ٱلۡحَكِیمُ }
«አላህ እንድህ ይላል፦» ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ከፍተኛ ባህሪይ(አንድነትና ለሱ ቢጤ ለሌለዉ መሆን)አለዉ ። እርሱም አሸናፊ እና ጥበበኛ ነዉ።{ አር_ሩም:27}
ᓂ የአላህ ስሞች ሁሉ እጅግ በጣም ዉቦች ናቸዉ።
ᓂ በእነሱ ማመን ሙስሊሞች ላይ ገደታ አለባቸዉ።
ᓂ የአላህ ስሞች ተዉቂፍያ ናቸዉ።
ᓂ ስሞቹ ከባህሪዉና ከስራዉ የተወሰዱ አይደሉም።
ᓂ የስሞቹ ቁጥር ብዛት አይታወቅም፤ በ99ብቻ አይገደብም።
ᓂስሞችን ማስተባበልና ማጣመም የለም።
ᓂ ስሞችን ማጣመም የሚሆነዉ ካፀደቁ በኋላ መካድ ወይም የሚያመላክቱትን ትርጉም መናድ።
ᓂ ወይም የአላህን ስሞች ከፍጡራን ስምና ባህሪ ጋር ማመሳሰል ነዉ ይህን ያደረገ ግልጽ ጠማማ ነዉ።
✍️ይቀጥላል ኢንሻ አላህ......
አንባቢ ሁን አንባቢ ስትሆን ከማይጠቅምህ ነገር ትርቃለህ ጊዜህን በመልካም ነገር ቢዚ ታደርጋለህ!!
⭚ ወደ ግሩፓችን ለመቀላቀል⤦⤦፦
t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed
t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed
⭚ ወደ ቻናላችን ለመቀላቀል ⤦⤦፦