Translation is not possible.

✍️أركان الإيمان !!

⏠⏠⏠⏠⏠

የእምነት መሠረቶች!!

⏡⏡⏡⏡⏡  

⏞⏞⏞

↳ ክፍል  ⓼↲

⏟⏟⏟

«በአላህ የጌትነት ባህሪ ማመን ከባለፈ የቀጠለ!!»

قال تعالى:{ وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءࣲ قَدِیرٌ }

«አላህ እንድህ ይላል፦ የሰማያትና የምድር ንግስና ለአላህ ብቻ ነዉ።አላህም በነገሩ ሁሉ ቻይ ነዉ። (አል ዒምራን :189)

قال تعالى:{ وَقُلِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ ٱلَّذِی لَمۡ یَتَّخِذۡ وَلَدࣰا وَلَمۡ یَكُن لَّهُۥ شَرِیكࣱ فِی ٱلۡمُلۡكِ وَلَمۡ یَكُن لَّهُۥ وَلِیࣱّ مِّنَ ٱلذُّلِّۖ وَكَبِّرۡهُ تَكۡبِیرَۢا }

«አላህ እንድህ ይላል፦ለዚያ ልጅን ላልያዘዉ ለርሱም በንግስናዉ ተጋሪ ለሌለዉ ለርሱም ከዉርደት ረዳት ለሌለዉ ለአላህ ምስጋና ይገባዉ ።በልም ማክበርንም አክብረዉ። (አል ኢስራእ:111)

قال تعالى:{ قُلۡ مَن یَرۡزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَاۤءِ وَٱلۡأَرۡضِ أَمَّن یَمۡلِكُ ٱلسَّمۡعَ وَٱلۡأَبۡصَـٰرَ وَمَن یُخۡرِجُ ٱلۡحَیَّ مِنَ ٱلۡمَیِّتِ وَیُخۡرِجُ ٱلۡمَیِّتَ مِنَ ٱلۡحَیِّ وَمَن یُدَبِّرُ ٱلۡأَمۡرَۚ فَسَیَقُولُونَ ٱللَّهُۚ فَقُلۡ أَفَلَا تَتَّقُونَ }

«አላህ እንድህ ይላል፦ ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነዉ ? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ  ማን ነዉ ?ከሙትም ሕያዉን የሚያወጣ ከሕያዉም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነዉ ? ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነዉ? በላቸዉ። በእርግጥም አላህ ነዉ ይሉሃል። ታድያ(ለምን ታጋራላችሁ ?) አትፈሩትምን? በላቸዉ ።(ዩኑስ:31)

قال تعالى:{ مَا ٱتَّخَذَ ٱللَّهُ مِن وَلَدࣲ وَمَا كَانَ مَعَهُۥ مِنۡ إِلَـٰهٍۚ إِذࣰا لَّذَهَبَ كُلُّ إِلَـٰهِۭ بِمَا خَلَقَ وَلَعَلَا بَعۡضُهُمۡ عَلَىٰ بَعۡضࣲۚ سُبۡحَـٰنَ ٱللَّهِ عَمَّا یَصِفُونَ }

«አላህ እንድህ ይላል፦ አላህ ምንም ልጅን አልያዘም  አልወለደም። ከእርሱም ጋር አንድም አምላክ የለም። ያን ጊዜ ሌላ አምላክ በነበረ)አምላክ ሁሉ በፈጠረዉ ነገር በተለየ ነበር። ከፊላቸዉም በከፊሉ ላይ በላቀ ነበር። አላህ ከሚገልፁት (ጎደሎ ባህሪ)ጠራ ።(አል ሙእሚኑን:91)

⎇እምነቱ በአላህ ጌትነት (ሩቡቢያህ) የተስተካከለለት  ሰዉ ወደ ቀጥተኛ መንገድ ይመራል፣ይህ እምነት ግን ብቻዉን አይጠቅመዉም። በአላህ አምላክነት (ኡሉሂያና)እና በመልካም ስሞቹ ባማሩ መገለጫ ባህሪዎቹ (አስማኡ_ወስ_ሲፋት) ማመን የግድ ይለዋል። በአላህ ጌትነት ሩቡቢያህ ብቻ ያመነ  ከሺርክ ጠራ አይባልም።  ምክንያቱም የመካ ሙሽሪኮችም አልካዱትምና ።

⎇ አላህ በጌትነት ብቸኛ ያደረገ፣አላህን በብቸኝነት ለመገዛት መንገዱ ተመቸዉ ፣አእምሮዉ ይፀዳል፣ልቡ ይረጋጋል፣በአላህ ዉሳኔ ፍርድ ይወዳል፣በአላህ ላይ ትክክለኛ መመካት ይመካል።

✍️ይቀጥላል ኢንሻ አላህ......

↳↴↷↴↷↴↷↴↷↴↷↴↷↴↷↲

t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed

t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed

Send as a message
Share on my page
Share in the group