Translation is not possible.

✨የቅርብ ሰዎችን ታገስ✨

የቅርብህ ሰዎች ስህተታቸው የጎላ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ከሩቆቹ ሰዎች ይልቅ አጠገብህ ያሉ ሰዎች ብዙ ስህተት ስላለባቸው ሳይሆን ስህተታቸውን በየጊዜው የማየት እድል ስላለህ ነው፡፡ በየቀኑ የሚወስኑትን ውሳኔ፣ የሚገልጡትን ስሜትና

የመሳሰሉት ስለምትመለከት በዚያው መጠን እነሱን ለመታገስ ካልወሰንክ የቅርቡን እየናቁ የሩቁን የማከበር ወጥመድ ውስጥ መግባትህ አይቀርም፡፡

ከዚህም በተጨማሪ፣ የቅርብ ወዳጆችህ ካላቸው ቅርበት የተነሳ ራሳቸውን ግልጽ አድርገው የመቅረባቸውም ሁኔታ የመናቅን ዝንባሌ ሊያሳድሩብህ ይችላል።

ሰዎችን ባወቁ መጠን ከመናቅ ይልቅ

መታገስና ማክበር የበሳሎች ምልክት ነው፡

t.me/hikem2

Send as a message
Share on my page
Share in the group