Translation is not possible.

ድንቅ ስራ

💦💦💦

በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውንና የመስገጃ ቦታዎችን የሚያመላክት መተግበሪያ(Application) ይፋ ሆነ!

አፕሊኬሽኑ "Musalla" የሚሰኝ ሲሆን ለአንድሮይድና ለ IPhone (IOS) ተጠቃሚያዎች የተዘጋጀና መተግበሪያው በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በአረብኛና በእንግሊዘኛ ቋንቋ አማራጮች መስራት የሚችል ነው።

ከመስገጃ ቦታዎች በተጨማሪ መስገጃ ቦታዎቹ የሴቶች መስገጃ፣ ውዱዕ ማድረጊያና የመኪና ማቆሚያ እንዳላቸው ወይም እንደሌላቸው የሚጠቁም እንዲሁም የመስጂዶችን አድራሻ በቪዲዮና በምስል ጭምር ማሳየት የሚችል አፕሊኬሽን ነው ይፋ የሆነው።

መተግበሪያው ከተማው ላይ ያሉ የቀብር ቦታዎችንና የመጅሊስ ፅህፈት ቤቶችን እንዲሁም የመስገጃ አቅጣጫ ቂብላ መጠቆም የሚችል ነው።

አሁን ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አብዛኛዎቹን ሙሰላዎችን እና መስጂዶችን ያካተተ ሲሆን ፤ እርሶ የሚያውቁትን የቀሩ ቦታዎችን እንዲሁም ከአዲስ አበባ ውጪ የሚገኙትን መስጂዶችና ሙሰላዎችን በመጨመር በዚ መልካም ስራ ማገዝ ትችላለችሁ።

አፕሊኬሽኑን ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ አውርዳችሁ መጠቀም የምትችሉ ሲሆን ሌሎች እንዲጠቀሙበትም ሼር በማድረግ እንድታጋሩ እንጠይቃለን።

የአፕሊኬሽን መገኛ ሊንክ:- https://onelink.to/quvuv3

https://ummalife.com/adnankemal

image
image
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group