Translation is not possible.
#በአንድ_ቤት_የሚኖሩ_ሶስት_ዓይነ_ስውራን_ልጆች 😪
 
"ካሁን በኃላ ልጅ መውለድ አልፈልግም " ወላጅ እናት😭😭
 
የአንድ አባት ፣ የአንድ እናት ልጆች በአንድ ቤት የሚኖሩ ሶስት አይነ ስውራንን ወንድሞቻችን ላንፍሮ ወረዳ ሶስተሮ ቀበሌ ላይ ይገኛሉ
 
ሶስቱ ወንድማማቾች
1) ቃሲም ሙክታር - 24 ዓመት
2) ፉአድ ሙክታር - 15 ዓመት
3) መሀመድ ሙክታር - 6 ዓመት
 
ሲሆኑ ከልጅነት ጀምሮ ዓይነ ስውራን ናቸው ።
 
ታድያ እነዚህ ወንድሞች ዓይነ ስውር ብቻ ስለሆኑ የነገ ተስፋ የሌላቸው ፣ ከደሳሳ ቤታቸው ና ከሰፈራቸው ወጥተው የማያውቁ ። ከእናታቸው ጋር ቤት የሚውሉ 😪
 
ነገር ግን መማር የሚፈልጉ ፣ የነገ ተስፋቸውን ማሳመር የሚፈልጉ ወንድሞቻችን ናቸው
 
ዓይነ ስውርነት እርግማን አይደለም ❗️
ተምረው ፣ ተለውጠው ፣ የብዙሃንን ህይወት የቀየሩ ብዙ አይነ ስውራን በሀገራችንም በአለማችንም አሉ ።
 
ማህበረሰባቸው ተስፋ ሰጥቷቸው ፣ ከጎናቸው ሆኖ አበርትቷቸው የተሻለ ህይወት የሚገፉ አሉ
 
እነዚህንም ወንድሞቻችንን እናግዛቸው ና አሁን ካሉበት የተሻለ ህይወት እንዲመሩ እናድርግ 🙏
 
ምን እናድርግላቸው ?
1) ጦራ ከተማ ቤት ተከራይተን እናምጣቸው ፣
2) ት/ት እናስገባቸው ና ይማሩ
3) ቁርዓን ቤት ቁርዓን ቢቀሩ
 
ለዚህም
የቀለብ ፣ የቤት ኪራይ ፣ የቤት ቁሳቁስ ፣ የት/ት ቁሳቁስ እንፈልጋለን ....
 
የተሻለ ሀሳብ ካላችሁም እንመካከር ና ተጋግዘን ችግራቸውን እንፍታ
image
Send as a message
Share on my page
Share in the group