Translation is not possible.

ለምን ሳውዲን ብቻ?

የኢኽዋን ጫጩቶች የሆነ ነገር በተከሰተ ቁጥር ሳውዲንና ኡለሞቿን ለመተቸት ይሯሯጣሉ።

በኢስራኢልና በፍሊስጢንም ጉዳይ አይናቸውን ሳውዲ ላይ ቸክለዋል።ሚገርመው በዋነኝነት ትንኮሳው እንዲጀመር ያነሳሳችውን ኢራንን እንኳን ኣንድ ነገር ሲናገሩ አይታዩም።

ትንኮሳውን ለኩሶ እንደ አይጥ ጉድጓድ ውስጥ የተደበቀውንም ሀማስ አይናገሩም፣የፍሊስጢን ጎረቤት ሆነ እንኳን ድንበሯን ዘግታ ምታየውን ግብፅን አይናገሩም።

ሰሞኑንም የፍልስጢን ህፃናት እየሞቱ ሳውዲ የቦክስ ውድድር አካሄደች ብለው እየለፈለፉ ነው።

ወንድሜ የፍሊስጢ ዜጎች ሰላምም ቢሆኑ ኢሄንን ቦክስና በውስጡ ያሉ መዕሲያዎችን ሀላል አያረገውም፣ኢሄንን ነገር ከፍሊስጢን ህፃናት ጋር ማያያዝ የፈለከው ሰዎች ልብ ላይ የሰውዲን ጥላቻ ለማስገባት ካልሆነ በስተቀር ሌላ አላማ ዬለውም።

ሰሞኑን እራሱን ያአለም ሙስሊሞ ተወካይ ነኝ የሚለውና የናንተው ኡለማ ተብዬዎች ያቋቋሙት ድርጅት ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ግድ ይላል ብሎ ፈትዋ ሲሰጥ ከጠቀሳቸው ሀገሮች ውስጥ እኮ ሳውዲ ዬለችበትም ለምን እነሱን አትናገሩም?።

ሃማስ የመጀመሪያውን ጥቃት ፈፀመ ሲባል እኮ የጨፈራቹት እናንተ ናቹህ፣እኛማ ትዝ ያለን ኢሄንን ተከትሎ ሚመጣ በፍሊስጢንያውያን ላይ የሚደርሰው ሰቆቃ ነበር ትዝ ያለን።

ሃማስማ አጠቃ ተባለ ከዛ ጉድጓድ ውስጥ ገባ ፣የሞቱት ምንም እማያቁ እሱም ኢሄን ጥቃት ሲያደርስ ያላማከራቸው ንፁሃን ዜጎችና የአረብ ሀገራት ናቸው።

መውቀስ ከፈለክ ቅድሚያ ነብሲያህን ውቀስ ፤ካለህበት መእሲያ ወጥተህ ሸሪያው ካንተ ሚጠብቀውን ነገር ስራ፤ዱኣም አድርግ ከዛ ቦሃላ አላህ ድሉን ለማምጣት ሃማስም የአረብ ሀገራትም አያስፈልጉትም።

Copy

Send as a message
Share on my page
Share in the group