Abu Mame shared a
Translation is not possible.

ጋዛ እንደት ዋለች _

፨ ጦርነቱ በአየርም በምድርም በባህርም ተፋፍሞ ቀጥሏል ። እስራኤል ከባህርና ከአየር በሚሳኤል ከምድር ደግሞ በከባድ መሳሪያዎች ታግዛ ጋዛን እየደበደበች ትገኛለች ። ግና ንፁሀንን ከመፍጀት ያለፈ ስኬትን ማስመዝገብ ተስኗት እጅግ ከባድ መከላከል ገጥሟታል !

፨ በዛሬው እለት ሀማስ አንድን ከፍተኛ የእስራኤል የጦር አመራር ገድሏል ። ዛሬ ሀማስ የገደለው የእስራኤል ጦር መሪ የ 188ኛ መካናይዝድ ብርጌድ 53ኛ ባታሊዮን ዋና አዛዥ የሆነውን ሌተናል ኮሎኔል ሳልማን ሀባካን ነው ። ይህም እስራኤል ጦርነቱ ከተጀመረ በሗላ የተገደለባት ሌላኛው ትልቅ የጦር መሪ ሆኗል ። ይህ በእንድህ እንዳለ ዛሬ የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር በሰጠው መግለጫ ትላንትና ዛሬ የተገደሉት የእስራኤል ወታደሮች ቁጥር 22 መድረሱን አሳውቋል ።

፨ በአሁኑ ሰአት ጋዛ ላይ እጅግ አልህ አስጨራሽ ትንቅን እየተካሄደ ነው ። የእስራኤል ሚዲያዎች በአሁኑ ሰአት እያወጡት ባለው ዘገባ " ከዚህ በፊት ተደርጎ የማይታወቅ ጦርነት አጋጥሞናል ወታደሮቻችን እጅግ ከባድ ፈተና ውስጥ ይገኛሉ መላው እስራኤላዊያን ለወታደሮቻችን ፀልዩ " ሲሉ አሳውቀዋል ። አሁን ሀማስና እስራኤል የሞት ሽረት ትግል ላይ ናቸው ።

፨ ሀማስ ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ መሆኑን አሳውቋል ። " ያሲን " በተሰኜው ሚሳኤሉም በርካታ የእስራኤል ታንኮችን ማውደሙን አሳውቋል ።

፨ ሂዝቡሏህ በዛሬው እለት በፈፀመው ተደጋጋሚ የሚሳኤል ጥቃት በእስራኤል ከተሞች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል ። የእስራኤል ከተሞች በእሳት ተያይዘው ሲነዱ ታይተዋል ። ሂዝቡሏህ ይፋዊ ጦርነት ለማወጅ የሰይድ ሀሰን ነስረሏህን ትእዛዝ እየጠበቀ ነው ተብሏል ። እስካሁን ሂዝቡሏህ በርካታ ጥቃቶችን በእስራኤል ላይ ማድረሱን የቀጠለ ሲሆን እስራኤልም አፀፋውን እየመለሰች ነው ።

፨ የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር ዩአቭ ጋላንት " እንደዚህ አይነት ከባድ ጦርነት አልጠበቅንም ነበር " ብሏል ። እርሱ እንዳለው ሀማስ በማይጠበቅ መልኩ እጅግ ራሱን አደራጅቶና ለሁሉም ነገር ተዘጋጅቶ ነው የጠበቀን ብሏል ።

#seid_mohammed_alhabeshiy

Send as a message
Share on my page
Share in the group