Translation is not possible.

🔎📃

"የሁድ" የሚለው ስም መነሻ ምንድነው በሚለው ላይ 3 እይታዎች አሉ

① የሁድ የሚለው ስም የነቢዩላህ ያእቆብ አለይሂ ሰላም 4ተኛ ልጅ ከሆነው «የሆዛ» የተወሰደ ነው የሚሉ አሉ

② የሁድ የሚለው ስም በ922 bc አካባቢ ከነበረው የ«የሆዛ አስተዳደር» የተወሰደ ነው የሚሉ አሉ

[የየሆዛ አስተዳደር ከሱለይማን አለይሂሰላም መሞት ቡሀላ በደብቡ ፍልስጢን ራሳቸውን ያስተዳድሩ የነበሩ ህዝቦች ናቸው ህዝቦቹ የየሆዛ እና የቢንያሚን ዘሮች ናቸው እንደሚታወቀው የሆዛ እና ቢንያሚን የነቢዩላህ ያእቆብ አለይሂሰላም ልጆች ናቸው]

ስለዚህ ሁለቱ እይታዎች አንድ ባይሆኑ እንኳ ተቀራራቢነት አላቸው

③ ይህ ደግሞ ከኢስላም ኡለማኦች የተነሳ እና የተለየ እይታ ነው

እሱም ነቡዩላህ ሙሳ አለይሂሰላም በኑ ኢስራኢሎችን ለሰሩት ወንጀል ተውበት እንዲያደርጉ ሲያዛቸው ከፊሉ ከልባቸው ተፀፅተው ወደ አላህ ሲመለሱ የተወሰኑ ጭፍሮች ግን ተውበታቸው የውሸት ነበር እነሱ《 هودا》የሚል መጠሪያ ተሰጥቷቸዋል ያ የየሁድ መሰረት እና መነሻ ነው ይላሉ

ወላሁ አእለም

ምንጭ፧ 

*بنو إسرائيل واليهود

*فلسطين بين حقيقة اليهود واكذيبة التلمود

*خط الزمن

Send as a message
Share on my page
Share in the group