Translation is not possible.

በኒቃብሽ ኩሪ !

በሱረቱል አህዛብ በደማቅ ተከትቧል፤

ከአንገትሽ ቀናበይ  ታሪክሽ ተውቧል፤

ድንቅ ነው ኢስላምሽ ከአምላክ የተሰጠሽ፤

ቅይጥ የሌለበት ጥርት ያለ ሀብትሽ፤

እስኪ መለስ በይ እልፍ አመታትን፤

ትእዝዛ ሲመጣ ወህይ ከአምላካችን፤

እንዴት ነበረ እስኪ ድንቁ ታሪካችን፤

የሂጃቡ አያህ ሲወርድ ለአለማት፤

ያኔ ሲታዘዙ እኒያ ሶሀቢያት፤

ሀገሩን አስዋቡት በጥቁር ቀለማት፤

በኒቃብ በጅልባብ አበሩ በውበት።

〰〰〰〰〰〰〰〰〰

አንቺስ ምንሽ ሞኙ ማማር የምትጠይው፤

በሂጃብ ተውበሽ አምላክሽን ታዘዢው፤

አዎ ታዘዢው ሀያሉን ህልምሽ እንዲሳካ፤

በዱንያም በአኼራም እንድትይ ፈካ፤

አትስጊ በፍፁም ባል ይጠፋል ብለሽ፤

እዝነቱን ፈልገሽ ኒቃብ በመልበስሽ፤

አንቺ ጀግና ሆነሽ ለትእዛዙ ካደርሽ፤

ቤትሽን ያንኳኳል ይቆማል ከበርሽ።

〰〰〰〰〰〰〰〰

ኢልምሽን ተማሪ ጠዋት ማታ ድከሚ፤

ጅህልናን ለመግፈፍ በደሊል ታከሚ፤

በሰላሙ ጊዜ ስንቅሽን ካልሰነቅሽ፤

ጎታችሽ ይበዛል አንችም ትሄጃለሽ፤

ስለዚህ እህቴ ኢልም ላይ ጠንክሪ፤

አሰሱን ገሰሱን ቆሼ ፍርፋሪ፤

እንደ እስፓንጅ አትምጠጭ ፈጣሪሽን ፍሪ።

እውነቱን ልንገርሽ የኒቃብን ዋጋ፤

ሊያናግርሽ ያፍራል ካንቺ የተጠጋ፤

መናቅኮ አይደለም ክብር ስላለው ነው፤

ሊቀርብሽ ያልቻለው በሩቁ የሸሸው፤

አንቱታን አተረፍሽ በ15 አመትሽ፤

ድል አጎናፀፈሽ ኒቃብ በመልበስሽ፤

ወለም ዘለም አትበይ ፅኚ በሂጃብሽ፤

ፊትናም አትፍጠሪ ተደበቂ ቤትሽ፤

ምድር ሁኝ ለባልሽ ሰማይ እንዲሆንልሽ፤

ክብርን አጎናፅፊው እሱም እንዲያከብርሽ።

〰〰〰〰〰〰〰〰

ደሞ ሴቶች አሉ ፀጉር የሚቆልሉ፤

ሂጃብ ለበስን ብለው የሚንቀዋለሉ፤

ረሱል ተራግመዋል ብለሽ ስትነግሪያቸው፤

አቦ አታጠባብቂ እነሱን ተያቸው፤

ገና አልሰለጠኑም ኃላ ቀር ናቸው፤

ብለው ያሾፋሉ ሞኛ ሞኝ ናቸው፤

ፀጉር መቆለሉ ደሞም መወጣጠር፤

ቅርፅን ማሳየቱ ሂጃብን መወርወር፤

ይሄ አይደል መስፈርቱ ለትዳርሽ መስመር፤

ይልቅማ አዳምጪኝ ለትዳርሽ ማማር፤

ዘላቂው መፍትሄ በሰላም ለመኖር፤

ሁሌ ለመወደድ ሁሌም ለመፈቀር፤

ሂጃብ ነው ሚስጥሩ ልቀቂው ከላይሽ፤

ሀያእም ተላበሽ አርጊው ጎረቤትሽ፤

ፈላስፋም አትሁኝ ማስረጃን ሰንቂ፤

ለምትሰሪው ስራም ደሊሉን እወቂ፤

ይህንን ካደረግሽ እህቴ እወቂ፤

ፍፁም አትወድቂም የለሽም ነቅናቂ።

Send as a message
Share on my page
Share in the group