Terjemahan tidak mungkin.

ነብዩ ሰዐወ እንዲ ብለዋል:- «የተራበቡ ሰዎች በሰሃን ወደ ቀረበው ምግብ ሊበሉ አንደሚሰባሰቡት (እንደሚጠራሩት) ህዝቦች (ከሃዲዎች) በናንተም ላይ ይጠራሩባቹሃል!»

ከሶሃቦች መካከልም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ እንዲህ የሚተባበሩብን ያን ግዜ እኛ በቁጥር አናሳ ስለሆንን ነውን? "

ረሱሉም «እንደውም ያኔ ብዙ ናችሁ ነገር ግን ጎርፍ ሰብስቦ እንደሚያመጣው የተበታተናችሁ ግሳንግስ (የጎርፍ ላይ አረፋ) ናችሁ! አላህም ጠላቶቻችሁ እናንተን የመፍራትን ግርማ ያነሳላቸዋል በናንተ ልብ ውስጥ "ወህን" ን ይጥልባቹሃል! አሉ

ሶሃቢዪም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ ወህን ምንድነው? ብሎ ጠየቃቸው

ረሱሉም "ወህን ማለት ዱንያን መውደድና ሞትንም መጥላት ብለው መለሱ»

(صحيح أبي داود 4297)

image
Hantar sebagai mesej
Kongsi di halaman saya
Kongsi dalam kumpulan