Translation is not possible.

በብሊንከን ላይ የቀረበው ተቃውሞ የህዝብን ቁጣ ማስተንፈሻ?

Medea Benjamin በፀረ-ጦርነት ተቃውሞ ትታወቃለች።ፀረ ጠርነት ተቃውሞ ከሚያሰሙ ተባባሪዎቿ ጋር Blinken ላይ ተቃውሞን አስምታለች። ጭልፊቱ CNN እና ሌሎችም ሚዲያዎች ወሬውን ለአለም አድርሰዋል።

Medea Benjamin የሆነ አዳራሽ ስትገባ ለምን እንደሆነ ይታወቃል።በየሊብራል ሚዲያው የምትጋበዝ የተለያዩ ባለስልጣናት ላይ ተቃውምን የምታሰማ ትጉህ አክቲቪስት ናት።ፍልስጤማውያንን በመደግፍ ትታወቃልች።የኢራቅን ጦርንት በመቃወም ትታወቃልች።Blinkenንን እርሷና ባልደረቦቿ ተቃወሙ የሚለው ነገር ሲጋነን አየሁት።

Medea Benjamin ስፍራው ላይ ከታየች የካፒታል ፖሊስ ለመቃወም መግባቷን አያውቅም ማለት አይቻልም። ፊትን መለያ ቴክኖሎጂው( face recognition technology) የትም ብትሔድ ያውቃታል። ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር Blinken ጀርባ ስትቀመጥ እንደ አይሁድም እንደ አሜሪካ ባለስልጣንም እስራኤልን ደግፋለሁ ላለው Blinken ለማጨብጨብ ሳይሆን ንግግሩን ለማቋረጥ መሆኑ ይታወቃል። ብዙ ግዜ በፖሊስ ተጎትታ ነው ከአዳራሽ የምትወጣው። ይህ አዲስ አይደልም። ባይሆን የርሷና የባልደረቦቿ ተቃውሞው የሚጠበቅ ነው። ግን ጨቋኙና አጥፊው ሐይል በአለም ላይ ላሉ የፍልስጤም ደጋፊዎችን ለማማለልና ለማስደሰት ሊጠቀምበት ይችላል ብሎ መናገር አይገድም። የርሷና የተባባሪዎቿ ተቃውሞ ከBiden ካቢኔ ፖሊሲ ላይ አንዲትን ፊደል የመፋቅ ሐይል የለውም። እና አረጋጉት።

በጋዛ ውስጥ በፍልስጤማውያን ላይ የሚከናወነውን ዘር የማፅዳት ወንጀል ለሰአታት ትንሽም ቢሆን ለማስረሳት ቀጣፊ አለም አቀፍ ሚዲያዎች የርሷን ፊት ደጋግመው እንዳያሳዩ ሰጋለሁ።

ልብ ያለው ልብ ይበል!

Send as a message
Share on my page
Share in the group