Translation is not possible.

የደላው  መች  ቀረ......

    

ሁሉም ይሞታታል አስጠላም አማረ

ሁሉም  ይጓዛታል ያቺን  የሩቅ ጉዞ

የሌለው ባዶውን ያለው ስንቁን ይዞ

ዛሬማ ምን አለ ባይሰግዱ ባይፆሙ

ይቸግራል  እንጂ  አላህ  ፊት ሲቆሙ

ዛሬማ  ምን  አለ  ቢጠጡ  ቢሰክሩ

ይቸግራል  እንጂ  ሙተው  ሲቀበሩ

ዛሬማ  ማን  አለ   የሚያጋልጥህ

ከቀብር  ስትገባ  ይታያል  ጉድህ ።

    

Send as a message
Share on my page
Share in the group