Translation is not possible.

ሶላትህ ምን ይመስላል?

አሰጋገድህስ እንዴት ነው?

ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

📎«የሙናፊቆች ሶላት የአካል "እንቅስቃሴ" ብቻ ነው። የቀልብ "በኹሹእ የሚሰገድ" ሶላት አይደለም።»

📎 አላህ የሙናፊቆችን ሶላት በተመለከተ እንዲህ ይላል።

…وَإِذَا قَامُوا إِلَى الصَّلَاةِ قَامُوا كُسَالَىٰ يُرَاءُونَ النَّاسَ وَلَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ إِلَّا قَلِيلًا

«ወደ ሶላትም በቆሙ ጊዜ የተሰላቹ ሆነው ስዎችን የሚያሳዩ ኾነው ይቆማሉ፡፡ አላህንም ጥቂትን እንጅ አያወሱም፡፡

(ሱረት አል-ኒሳእ - 142)»

✅በተቃራኒው የሙእሚኖች ሶላት በተመለከተ ጌታችን አላህ እንዲህ ብሏል።

قَدْ أَفْلَحَ الْمُؤْمِنُونَ () الَّذِينَ هُمْ فِي صَلَاتِهِمْ خَاشِعُونَ

✅«ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)፡፡ እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች፡፡»

(ሱረት አል-ሙእሚኑን 1- 2)

✅ኹሹእ የሶላት ሩህ ነው። መስገድህ ካልቀረ አላህን በመፍራትና በመተናነስ እያስተዋልክ በስነስርአት ስገድ።

http://t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed

image
Send as a message
Share on my page
Share in the group