ዲቪ መሙላት እንደት ይታያል⁉️
=====================
✍ ባለፈ እሁድ በኢማሙ አሕመድ መስጅድ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ በነበረው የፈታዋ ፕሮግራም ላይ መልስ ከሰጠባቸው ጥያቄዎች አንዱ ወደ ሃገረ አሜሪካ ለመሄድና ነዋሪ ለመሆን የሚሞላውን የዲቪ እጣ (DV Lottery) በተመለከተ ነበር።
ጉዳዩ የብዙዎቻችሁም ጥያቄ ይሆናል ብዬ ስላሰብኩ ቃል በቃል ባይሆንም የመልሱን ጭብጥ ላጋራችሁ።
ሐቂቃ ወደ ኩፍ'ር ሃገር ሂዶ በነርሱ የፈሳድ ህግ ተገዢ ሆኖ ለመተዳደር መሄድ አይፈቀድም። ከዲን አንፃር እነርሱ ጋ ካለው ፈሳድ በአንፃሩ የኛ የተሻለ ነው። (ምንም እንኳ የኛም ሃገር በሸሪዓህ የሚተዳደር ባይሆንም!)
አንድ ሰው የቱንም ያክል በዲኑ ጠንካራ ቢሆንም እዛ ሲሄድ ያለው የፈሳድ ጫና ከመክበዱ የተነሳ ሳያስበው ቀስ በቀስ እየተሸረሸረ ይሄዳል። በተለይ ደግሞ የልጆች ጉዳይ አሳሳቢ ነው። አንድ ሰው ለራሱ እዚህ የሆነ የዲን ግንዛቤ ኖሮት በዛ ጥንካሬው እቋቋማለሁ ብሎ ቢያስብ እንኳ እዛ ሂዶ ልጅ ከወለደ በኋላ ግን፤ ያለው የሃገሪቱ ህግ ወላጅ በልጁ ላይ እንኳ መብት እንዳይኖረው ተደርጎ የተደነገገ ስለሆነ ልጆችን በመልካም ኢስላማዊ አስተዳደግ ለማኖር ይከብዳል።
ስለዚህ የምንሄደው መቼም ዱንያን ፍለጋ ስለሆነ ያ ዱንያ ዲንን የሚያሳጣ ከሆነ ከነ ድህነታችን ይሄው ሃገራችን ይሻለናል።
(በተለይም ይሄ ከቅርብ ጊዜ በኋላ የጀመሩት ወላጆች የልጆቻቸውን እንኳ ጾታ መምረጥ አይችሉም ተብሎ ህፃናቱ ራሳቸው ናቸው ሲያድጉ ጾታቸውን የሚመርጡት ተብሎ የተደነገገው ነገር፤ በተለያዩ የትምህርት አይነቶቻቸው ላይ የሰገሰጉት የፈሳድ ጉዳይ፣ ለምሳሌ፦ ግብረ ሶዶማዊነትን ከመብት መቁጠር፣ እምነት አልባነትን… ወዘተ የልጆችን ለጋ አስተሳሰብ ይቀይራል። ገና አስተሳሰባቸው ሳይጎለብት ይሄንና መሰል ፈሳዶችን እየተጋቱ ያደጉ ልጆች ወላጆች ላስተካክላቸው ቢሉ እንኳ አይችሉም።
ይሄንን ደግሞ በደንብ የሚያውቁት እዛው ውጭ ላይ ያሉ ልጅ ያላቸው ወላጆች ናቸው። ሌላው ቀርቶ ኢስላማዊ ት/ቤቶች ራሱ ይሄንና መሰል ነገሮች ከመተዳደሪያቸው ውስጥ አስገብተው እንዲተገብሩ በሃገሪቱ ህግ ጫና የሚደረግባቸው አሉ። አሜሪካ ብቻ ሳይሆን እንደ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ደንማርክና መሰል የአውሮፓ ሃገራት ላይም ይህ አይነት ፈሳድ በብዛት ስላለ በተለይም ለልጁና ለሚስቱ የወደፊት ህይዎት የሚቆረቆር ወላጅ ወደነዚህ የፈሳድ ሃገራት ለመኖር ባይመርጥ የተሻለ ነው።)
አላሁ አዕለም!
||
t.me/MuradTadesse