7 ай Тәрҗемәсе
Татарчага аудару мөмкин түгел.

ለምንድነው_መኖር_የደከመህ/ሽ ?

.

ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? በዚች ምድር ላይ ስትኖር ሞት ለማንም እንደማይቀር አስብ እንጂ እራስህን ለማጥፋት አትመኝ። አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ

☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡

☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡

☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡

☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡

☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ ታስፈልገናለህ፡፡

፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::"በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት መሞክር ማለት ነው፡፡

https://t.me/Darutewhide

Telegram: Contact @Darutewhide

Telegram: Contact @Darutewhide

كن سلفيا علـى الجادة(በፍትህ ላይ ቀጥ ያልክ ሰለፊ ሁን) አስተያየትና ጥቆማ ለመስጠት ? @AbuNuhibnufedlu
Send as a message
Share on my page
Share in the group